በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን የግሉን የሥጋ ኢንደስትሪ ለመደገፍ 1 ቢሊዮን ዶላር መደቡ


ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ የግብርና ሚኒስትር ፀሃፊ ቶም ቪልሳክ እና የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሜሪክ ጋርላንድ በሥጋ እና የዶሮ እርባታ ጉዳዮች ላይ ከገበሬዎች፣ የሥጋ አቅራቢዎች ጋር በቪዲዮ ኮንፈረንስ ሲወያዩ
ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ የግብርና ሚኒስትር ፀሃፊ ቶም ቪልሳክ እና የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሜሪክ ጋርላንድ በሥጋ እና የዶሮ እርባታ ጉዳዮች ላይ ከገበሬዎች፣ የሥጋ አቅራቢዎች ጋር በቪዲዮ ኮንፈረንስ ሲወያዩ

ዩናይትድ ስቴትስ በአገሪቱ ያሉትን የስጋ ሀብት ልማት አሰመልክቶ እያሻቀበ ያለውን ገበያ የሚከላከል ምንም ዓይነት ውድድር ባለመኖሩ የግሉን ዘርፍ ለመደገፍ 1 ቢሊዮን ዶላር ትመድባለች ሲሉ ፕሬዚዳንት ባይደን ትናንት በሰጡት መግለጫ ተናገሩ፡፡

የባይደን ውሳኔ የመጣው አሜሪካ ውስጥ የበሬ፣ የአሳማ ሥጋና የዶሮ ሀብቶችን አምራችነት ጠቅልለው የያዙት ጥቂት ድርጅቶች ገበያውን በመቆጣጠራቸው በደንበኞቻቸውና አከፋፋዮቹ ላይ ዋጋ በመቆለል ትርፍ እያጋበሱ በመምጣቸው መሆኑን ተመልክቷል፡፡

ፕሬዚዳንት ባይደን በንግግራቸው “ካፒታሊዝም ያለ ውድድር ካፒታሊዝም አይደለም፡፡ ብዝበዛ ነው፡፡ በሥጋና ዶሮ ኢንደስትሪ ውስጥ የምናየውም ይህንን ነው” ብለዋል፡፡

በቅርቡ በዋይት ኃውስ የተደረገው አንድ ጥናት እንደሚያሳየው እስከ 85 ከመቶ የሚሆነውን የአሜሪካን ከብቶችና ዶሮዎች ገበያ የተቆጣጠሩት አራት ድርጅቶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

የ1 ቢሊዮን ዶላሩ ድጋፍ ገለልተኛ የሆኑ ሌሎች የግል ተቋማትን ተወዳዳሪነት እንዲያግዝ መሆኑም ተነግሯል፡፡

XS
SM
MD
LG