በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የባይደን ወደ ኔቶ ስብሰባ መጓዝና ተጨማሪ ማዕቀቦች በሩሲያ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን

ፕሬዚዳንት ባይደን ዛሬ ረቡዕ ከኔቶ አባል አገራትና ከአውሮፓውያኑ አጋሮቻቸው ጋር በዩክሬን ጉዳይ ለመምከር ወደ ብራስልስ እያቀኑ ሲሆን ዩክሬንን በወረረችው ሩሲያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀቦችን ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የዋይት ኃውስ የደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ጄክ ሱሌቫን “ባይደን ከአጋሮቻችን ጋር በመገናኘት ያሉትን ማዕቀቦች የበለጠ በማጥበቅና በተጣሉት ማዕቀቦችም ላይ ጠንካራ አፈጻጸም መኖሩ እንዲረጋገጥ” የሚያደርጉ መሆኑን ጉዞውን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ነገ ሀሙስ የኔቶ ጉባኤ ላይ ንግግር እንደሚያደርጉ ተነግሯል፡፡

ዘለንስኪ ከጉባኤው በፊት አስቀድሞ በሰጡት መግለጫ፣ ምዕራባውያኑ መሪዎች በሩሲያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀቦችን እንደሚጥሉና ለዩክሬን ተጨማሪ እርዳታዎችን ይሰጣሉ ብለው እንደሚጠብቁ ተናግረዋል፡፡

ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረችበት ጊዜ አንስቶ የዩክሬን ኃይሎች ለመጀመሪያ ጊዜ የሩሲያን ኃይሎች መልሰው ማጥቃት መጀመራቸውና የሩሲያን ወታደሮች ኢላማ በማድረግ አንዳንድ የተወሰኑ ቦታዎቻቸውንም ማስመለስ መቻላቸው እየተነገረ መሆኑ ተዘግቧል፡፡

የዩክሬን መከላከያ ሚኒስቴር ባለፈው ማክሰኞ የዩክሬን ጦር የዋና ከተማዪቱ ኪየቭ ክፍለ ከተማ የሆነችውን ማካሪቭን ከከባድ ውጊያ በኋላ መልሶ መቆጣጠሩን አስታውቋል፡፡

የዩክሬን ሰራዊት ከካርኪቭ በስተደቡብ ምስራቅ 120 ኪሜ ርቀት ላይ የምትገኘው አዚዩም የተባለችውን ከተማና በደቡብ ዩክሬን የከረሶን ከተማ አካባቢዎችን ለመቆጣጠር መልሶ ማጥቃት ለመጀመር መቃረባቸው ተነገሯል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ስለ ዩክሬን ስለምታደርጋቸው እነዚህ ጥረቶች ምላሽ ከመስጠት የተቆጠቡ ሲሆን፣ በአንዳንድ የአገሪቱ አካባቢዎች ግን ወደ ዩክሬን የሚያጋድሉ አዝማሚያዎች መታየታቸውን ገልጸዋል፡፡

የባይደን ወደ ኔቶ ስብሰባ መጓዝና ተጨማሪ ማዕቀቦች በሩሲያ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:00 0:00

የፔንታገን ቃል አቀባይ፣ ጆን ከርቢ፣ ባለፈው ማክሰኞ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ “አሁን ዩክሬናውያኑ መልሰው ወደ ማጥቃት የመሸጋገር ምልክት ማሳየታቸውን እየተመለከትን ነው” ብለዋል፡፡

“ጥበብ በተሞላበት ሁኔታ እየተከላከሉ ነው” ያሉት ቃል አቀባዩ “በጣም ብልህነት በተሞላበት ሁኔታ መከላከል ያስፈልጋል ብለው በሚያምኑበት ቦታ ሁሉ የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም እየተካለከሉ ነው፡፡ አሁን አንዳንድ ቦታዎችን ለማስመለስ በተለይ በደቡብ በኩል በከኸረስን አቅራቢያ ሙከራዎችን ሲያደርጉ እየተመለከትን ነው” ብለዋል፡፡

ሌሎች የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ደግሞ ከዚህም ገፋ ያለ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

የዋይት ሀውስ የደህንነት አማካሪው ጃክ ሱሌቫን ለጋዜጠኞች ሲናገሩ “ሩሲያ እስካሁን ያሳየቸው ያልተሳካላት መሆኑን ነው” ብለዋል፡፡ “ሩሲያውያኑ የፈለጉትን ከተማ ቢወስዱ የተፈለገውን ተጨማሪ አካባቢዎችን ቢቆጣጠሩ የዩክሬንን ህዝብ ለማንበርከክ ያስቀመጡትን የመጨረሻ ግባቸውን መቸም ቢሆን ሊያሳኩት አይችሉም ጠንካሮቹ ዩክሬኖች አልተበገሩም መልሰው እየተዋጉ ነው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ደግሞ በእንግሊኛ ቋንቋ በሚያሰራጨው መልዕክቱ የሩሲያ ኃይሎች ብዙ ዩክሬናውያን ሸሽተው በወጡባቸው ደቡባዊ ዩክሬን አካባቢዎች ያገኟቸው ስኬቶችን በመዘርዝር አድናቆቱን ይገልጻል፡፡

የዩክሬን ነዳጅ ማጠራቀሚያዎችና፣ ረጅም ርቀት ኢላማቸውን አነጣጥረው መምታት የሚችሉ የጦር መሳሪያዎችን መቆጣጠሩን ያመለክታል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የመረጃ ምንጮች የሩሲያ ወረራ ለሩሲያ ጦር ብዙ የአቅርቦት ችግሮችን እያመጣ ሲሆን የሩሲያ ጦር፣ የነዳጅ፣ የምግብ እና አቅጣጫዎችና ኢላማዎቻቸውን በትክክል የሚያመለክቱ መሳሪዎች እጥረት እየገጠማቸው መሆኑን ያመለክታሉ፡፡

XS
SM
MD
LG