በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጆ ባይደን ወደ ዊስከንሰኗ ከኖሻ ከተማ ይጓዛሉ


ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ የዲሞክራቲክ ፓርቲው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዕጩ ጆ ባይደን
ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ የዲሞክራቲክ ፓርቲው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዕጩ ጆ ባይደን

የዩናይትድ ስቴትስ የዲሞክራቲክ ፓርቲው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዕጩ ጆ ባይደን ዛሬ ወደ ዊስከንሰኗ ከኖሻ ከተማ ይጓዛሉ።

በጉዟቸው ህዝባዊ ስብስባ አድርገው ነዋሪዎችን ያነጋግራሉ። የምረጡኝ ዘመቻቸው ባወጣው መግለጫ ባይደን የሚጓዙት አንድ መቶ ሺህ ነዋሪዎች ባሏት ከተማ አሜሪካውያን ለማቀራረብ እና ለተደቀኑት ፈተናዎች አብሮ መፍትሄ ለመፈለግ እንደሆነ ገልጻል። ፕሬዚዳንት ትረምፕ ኪኖሻን ከሁለት ቀናት በፊት ጎብኝተዋል።

XS
SM
MD
LG