በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን በሠራተኞች ቀን ስለ አሜሪካውያን ሠራተኞች ክብር ይናገራሉ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በየዓመቱ በሚከበረው የሠራተኞች ቀን በዓል ላይ ለመካፈል ዛሬ ሰኞ ወደ ዊስካንሰን እና ፔንስልቬኒያ ክፍለ ግዛቶች መሄዳቸው ተነግሯል፡፡

ባይደን በዊንካንሰን ሚልዋኪ እና በፔንሴልቬንያ ፒትስበርግ ከተሞች ተገኝተው ስለ “አሜሪካውያን ሠራተኞች ክብር” ንግግር እንደሚያሰሙ የዋይት ሀውስ ቤተመንግሥት አስታውቋል፡፡

ከፕሬዚዳንቱ ጋር የሥራ ሚኒስትሩ ማርቲ ዎልሽ አብረው እንደሚጓዙም ተመልክቷል፡፡

የካፍሊፎኒያ ክፍለ ግዛት፣ የግብርና ሠራተኞች በሠራተኞ ማህበር ምርጫ ድምጽ የሚሰጡባቸውን መንገዶች ለማስፋት ለወሰደው እርምጃም ድጋፋቸውን እንደሚሰጡ ባይደን ትናንት እሁድ በሰጡት አስተያየት አስታውቀዋል፡፡

“መንግሥት ሠራተኞች እንዳይደራጁ የሚያደርጉ መሰናክሎችን ማቆም ሳይሆን ማስወገድ ይገባዋል፡፡ ህብረታቸውን መመስረት አለመመሰረቱን ግን መወሰን ያለባቸው ሠራተኞች ራሳቸው መሆን አለባቸው” ብለዋል ባይደን፡፡

የካሊፎኒያ ህግ አውጭዎች፣ ሠራተኞች ድምጻቸውን በፖስታ ቤት አማካይነት መስደድ እንዲችሉ የቀረበውን የህግ ረቂቅ አጽድቀዋል፡፡

የካሊፎኒያ አገረ ገዢ ጋቪን ኒውሰም ግን፣ የህግ ረቂቁ የምርጫውን ተአማኒነት ለመከላከል መወሰድ የሚገባቸው አስፈላጊ እምርጃዎች የሉትም ሲሉ፣ አሁን ባለበት ቅርጹ እንደማይቀበሉት ቃል አቀባያቸው አመልክተዋል፡፡

በየዓመቱ ሰኞ ቀን ላይ የሚውለው የሠራተኞች ቀን፣ በዩናይትድ ስቴትስ ለመጀመሪያ ጊዜ መከበር የተጀመረው እኤአ በ1894 መሆኑ ተዘግቧል፡፡

ምንም እንኳ በኦፊሴል ባይገለጽም፣ እለቱ የሠራተኞች ቀን የበጋው ወቅት የሚያበቃበት፣ ለተጓዦች ከቅዳሜ እስከ ሰኞ ረጅም የእረፍት ቀን ሆኖ የሚውልበትና ለብዙዎቹ ህጻናት የትምህርት ዘመናቸው የሚጀምርበትን ቀን ሆኖ እንደሚወሰድ ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG