በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን የአሜሪካን የዛሬ ሁኔታ የሚዳስሰውን ዓመታዊ ንግግራቸውን ዛሬ ምሽት ያደርጋሉ


ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን
ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን

ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ዛሬ ሐሙስ የካቲት 28 ማታ በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤቶች የጋራ ጉባኤ የአሜሪካ የዛሬ ሁኔታ የሚዳስሰውን ዓመታዊ ሪፖርት የሚያቀርቡበትን ንግግር ያደርጋሉ። ፕሬዚደንቱ በንግግራቸው አስተዳደራቸው ያከናወናቸውን ሥራዎች አስመልክተው ማብራሪያ የሚሰጡ ሲሆን የምክር ቤቱ አባላት የደህንነት ርዳታ የሚመለከተውን ሕግ እንዲያጸድቁ ግፊት ያደርጋሉ። በመጪው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ዳግመኛ ለመመረጥ በያዙት ጥረት መራጮች እንዲደግፏቸው በዛሬ ምሽት ንግግራቸው ተማጽኖ እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል።

ፕሬዚደንቱ ትናንት ረቡዕ በማኅበራዊ መገናኛዎች በቪዲዮ በቀረበው ንግግራቸው “ስለእርምጃዎቻችን እናሳውቃችኋለን። ለወደፊት ያለንን ዕቅድም እንነግራችኋለን” ብለዋል። ባይደን በመሠረተ ልማት፣ በመድሃኒት ዋጋ፣ በተማሪዎች የትምህርት ክፍያ ዕዳ እና በመሣሪያ ቁጥጥር ላይ ያተኮሩ ማብራሪያዎችን እንደሚሰጡ ይጠበቃል።

ፕሬዚደንት ባይደን የዘንድሮውን የአሜሪካ የዛሬ ሁኔታ ሪፖርት ማቅረቢያ ንግግራቸውን የሚያደርጉት በመጪው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ከቀድሞው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ጋራ ለሁለተኛ ጊዜ እንደሚፎካከሩ ከዕለት ወደ ዕለት ግልጽ እየሆነ በመጣበት ባሁኑ ወቅት መሆኑ ነው፡፡

ከፕሬዚደንት ጆ ባይደን ንግግር በኋላ የአላባማ ሴኔተር ኬቲ ብሪት የሪፐብሊካኖችን ምላሽ ያቀርባሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG