በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን ትረምፕን አነጋገሩ፣ ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር እንደሚኖር አረጋገጡ


ተሰናባቹ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን
ተሰናባቹ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን

ተሰናባቹ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር እንደተነጋገሩ እና ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንደሚደረግ ያረጋገጡላቸው መሆኑን ተናገሩ፡፡

ባይደን ዛሬ ሐሙስ በዋይት ሀውስ ባሰሙት ንግግር "ትላንት ተመራጩን ፕሬዝደንት ትራምፕን በማሸነፍዎ እንኳን ደስ ያለዎ ለማለት አነጋግሬያቸዋለው፣ መላ አስተዳደሬ ከቡድናቸው ጋር በመሆን ሰላማዊ እና ሥርዓት ያለው ሽግግር እንዲኖር አረጋግጨላቸዋለሁ።" ብለዋል፡፡.

ባይደን ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስን የመሩትንም የምርጫ ዘመቻ አድንቀዋል።

ባይደን የአሜሪካን ህዝብ ፍላጎትና ምርጫ እንደሚቀበሉም ተናግረዋል።

“ሀገሪቱ አንዱን ወይም ሌላውን ትመርጣለች፣ ሀገሪቱ የምትመርጠውን ምርጫ እንቀበላለን። ብዙ ጊዜ ተናግሬያለሁ “ሀገርህን ስታሸንፍ ብቻ መውደድ አትችልም፡፡” ብለዋል፡፡

ባይደን የአሜሪካ ምርጫ "ታማኝ ነው፣ ፍትሃዊ እና ግልጽ ነው፣ በማሸነፍም ሆነ በመሸነፍ ጊዜ ሊታመን ይችላል" ይችላሉ ሲሉ ስለ ምርጫው ተአማኒነት ተሟግተዋል።

አሜሪካዊያን “የዜግነት ግዴታቸውን እንደተወጡት፣ እኔም እንደ ፕሬዝዳንት ኃላፊነቴን እወጣለሁ። መሐላዬን እፈጽማለሁ፣ ሕገ መንግሥቱንም አከብራለሁ። እኤአ ጥር 20፣ እዚህ አሜሪካ ውስጥ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እናደርጋለን። ብለዋል፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG