በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን ስለ አየር ንብረት ለውጥ እና አፍሪካን አቋራጭ ባቡር ስለመገንባት ተናገሩ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን
የቡድን-7 እና ቡድን-20 አባል ሀገራት፣ የአፍሪካን አህጉር የሚያቋርጥ ባቡር ሊገነቡ የሚችሉበት አጋጣሚ ሊኖር እንደሚችል፣ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ተናገሩ፡፡
ፕሬዚዳንቱ ይህን የተናገሩት፣ በትላንት እሑድ የቬዬትናሙ ጉብኝታቸው፣ የአየር ንብረት ቀውስንና የምግብ እጥረትን አስመልክቶ በተካሔደው ውይይት ላይ ነው፡፡
ባይደን ስለ ባቡር መስመር ዝርጋታ ሲናገሩ፣ “ከተነሡት ነገሮች ውስጥ አንዱን፣ ከረጅም ጊዜ በፊት፣ ለቡድን-7 ጉባኤ አቅርቤ ነበር፡፡ አሁን በቡድን-20 ውስጥ ፍሬያማ ይኾናል፡፡ በአፍሪካ አህጉር በሙሉ፣ የባቡር ሐዲድ ግንባታችን ይረጋገጣል፤” ብለዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት የአፍሪካ ሀገራት፣ እንደ ምግብ ያሉ ሀብቶችን ለማከፋፈል የሚያስችላቸው፣ አህጉሪቱን የሚያካልል ምንም ዐይነት የአውራ ጎዳናም ኾነ የባቡር መንገድ እንደሌለ፣ ባይደን ተናግረዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ አያይዘውም፣ “የሰውን ልጅ ከኒውክሌር ጦርነት የበለጠ የሚያስፈራው ብቸኛው የህልውና ስጋት፣ የዓለም ሙቀት በቀጣዮቹ 20 እና 30 ዓመታት ውስጥ፣ ከ1ነጥብ5 ዲግሪ በላይ መጨመር ነው፤” ሲሉ፣ አስከፊ ችግር እንደሚያጋጥም አመልክተዋል፡፡ “ከዚያ የምናመልጥበትም መንገድ የለም፤” ሲሉም በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ጥረት እንዲደረግ አሳስበዋል

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG