በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ቬትናምን ጎበኙ


ፕሬዝደንት ጆ ባይደን በቬትናም ኮሚኒስት ፓርቲ ዋና ጸሃፊ ጉየን ትሮግ በሃኖይ አቀባበል ሲደረግላቸው (ፎቶ ኤኤፍፒ መስከረም 10፣ 2023)
ፕሬዝደንት ጆ ባይደን በቬትናም ኮሚኒስት ፓርቲ ዋና ጸሃፊ ጉየን ትሮግ በሃኖይ አቀባበል ሲደረግላቸው (ፎቶ ኤኤፍፒ መስከረም 10፣ 2023)

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ዛሬ ቬትናምን ጎብኝተዋል። በጉብኝታቸው ወቅትም ሁለቱ ሀገራት የኤሌክትሪክ አስተላላፊ መሣሪያዎችን (ሰሚኮንዳክተርስ) ማምረት እና ማዕድናትን በተመለከተ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

ቬትናም ከቻይና እና ከሩሲያ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግኑኝነት እያሳደገች ባለበት ወቅትም፣ በተመሳሳይ ከአሜሪካ ጋር ያላትን ግኑኝነት ከፍ አድርጋለች ሲል ሮይተርስ በዘገባው አመልክቷል።

ከአምሳ ዓመታት በፊት ከተደረገ አስከፊ ጦርነት በኋላ ቬትናም የተገኙት የአሜሪካው ፕሬዝደንት፣ በገዢው ፓርቲ በሃኖይ ከተማ ደማቅ አቀባበል ሲደረግላቸው፣ ተማሪዎች የአሜሪካንን ባንዲራ ሲያውለበልቡ ተስተውለዋል።

ከቻይና የሚገኘው አቅርቦት አስተማማኝ ባልሆነበት ወቅት፣ አሜሪካ አምራቿን ቬትናም እንደ ቁልፍ ሀገር ትመለከታለች፡፡ ጉብኝቱ የኤሌክትሪክ አስተላላፊ መሣሪያዎችን በተመለከተ ትኩረት የተደረገበት ሲሆን፣ ከጉግል፣ ኢንቴል፣ ቦይንግ እና ሌሎችም ታላላቅ ኩባንያዎች የተውጣጡ ኃላፊዎች ከቬትናም የቴክኖሎጂ መሪዎች ጋር ምክክር እንደሚያደርጉ ታውቋል። ///

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG