በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን ከዩክሬይን ጋር አዲስ የጸጥታ ስምምነት ተፈራረሙ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን እና የዩክሬይን ፕሬዚደንት ቮሎዶሚር ዜለንስኪ ለአስር ዓመታት የሚዘልቅ የጸጥታ ስምምነት ትላንት ሐሙስ ተፈራርመዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን እና የዩክሬይን ፕሬዚደንት ቮሎዶሚር ዜለንስኪ ለአስር ዓመታት የሚዘልቅ የጸጥታ ስምምነት ትላንት ሐሙስ ተፈራርመዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን እና የዩክሬይን ፕሬዚደንት ቮሎዶሚር ዜለንስኪ ለአስር ዓመታት የሚዘልቅ የጸጥታ ስምምነት ትላንት ሐሙስ ተፈራርመዋል።

ጣሊያን ውስጥ እየተካሄደ ካለው የቡድን ሰባት የመሪዎች ጉባዔ ጎን የተፈረመው ስምምነት የዩክሬይን የመከላከይ ኃይሎች የሩስያን ወረራ የመመከት ዓቅም ለማጠናከር የታለመ መሆኑ ተመልክቷል።

ቀጣይ የዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደሮች የቀድምው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ በመጪው ምርጫ ቢያሸንፉ እንኳን ጭምር ዩክሬይንን እንዲረዱ ግዴታ የሚያደርግ መሆኑን የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ገልጸዋል።

"ዓላማችን የዩክሬይንን የመከላከያ ዓቅም በዘላቂነት ማጠናከር ነው" ያሉት ፕሬዚደንት ባይደን "የዩክሬይን ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ ያለበት አሁን ባላት ጥቃትን የመከላከል አቅም እንዲሁም ወደፊትም የሚከሰቱ ወረራዎችን ለመመከት በሚኖራት ብቃት ላይ ሊሆን ይገባል" ብለዋል።

ስምምነቱ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ በሚያስፈልጉ እርምጃዎች ላይ ያተኮረ እንደመሆኑ መላውን ዓለም የሚጠቅም ነው። ሩስያ ዩክሬይን ላይ የምታካሂደው ጦርነት በመላው ዓለም ላይ የተደቀነ ተጨባጭ ስጋት ስለሆነ"

የዩክሬይን ፕሬዚደንት በበኩላቸው "ስምምነቱ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ በሚያስፈልጉ እርምጃዎች ላይ ያተኮረ እንደመሆኑ መላውን ዓለም የሚጠቅም ነው። ሩስያ ዩክሬይን ላይ የምታካሂደው ጦርነት በመላው ዓለም ላይ የተደቀነ ተጨባጭ ስጋት ስለሆነ" ብለዋል።

በስምምነቱ ላይ እንደተጠቀሰው ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬይን የጦር መሣሪያዎች፥ የተተኳሾች እና የስለላ መረጃዎች ማጋራት ድጋፍ ታደርጋለች። ስምምነቱ ዩክሬይን ወደፊት የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት አባል እንድትሆን የሚያመቻች እርምጃም እንደሚሆን ተመልክቷል።

ከዚህም ሌላ ጣሊያን ውስጥ ጉባዔ ላይ ያሉት የቡድን 7 መሪዎች ለዩክሬይን የ50 ቢሊዮን ዶላር ብድር ለመስጠት በመርህ ደረጃ ትላንት ሐሙስ ተስማምተዋል። የብድሩ ዕዳ የሚከፈለው ሩሲያ ዩክሬይን ላይ ወረራ በከፈተችበት ጊዜ በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት እንዳታንቀሳቅስ ከታገደባት ገንዘብ በሚገኘው ወለድ እንደሚሆን ተጠቁሟል።

በሌላ በኩል የዩክሬይን ጦርነት መቀጠሉን በተመለከተ የነቀፌታ አስተያየት የሚሰጡት የቀድሞው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ በአንድ ወቅት "እኔ አስተዳደሩን በተረከብኩ በመጀመሪያው ቀን አስቆመዋለሁ" ሲሉ ተደምጠዋል።

ትረምፕ ትላንት ሐሙስ በዋሽንግተን ከዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባላት ጋር የተገናኙ ሲሆን በሪፐብሊካን የኮንግሬሱ አባላት ድጋፍ ለዩክሬይን የጸደቀውን የ60 ቢሊዮን ዶላር እርዳት እንደነቀፉ የምክር ቤት አባላቱ ጠቁመዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG