በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን በጣሊያን የቡድን ሰባት አባል ሀገሮች መሪዎች ጉባዔ ናቸው


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ  ባይደን ዛሬ ሐሙስ በጣሊያን አፑሊያ ከተማ ከቡድን ሰባት አባል ሀገሮች መሪዎች ጋር ጉባዔ ላይ ናቸው፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ  ባይደን ዛሬ ሐሙስ በጣሊያን አፑሊያ ከተማ ከቡድን ሰባት አባል ሀገሮች መሪዎች ጋር ጉባዔ ላይ ናቸው፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ዛሬ ሐሙስ በጣሊያን አፑሊያ ከተማ ከቡድን ሰባት አባል ሀገሮች መሪዎች ጋር ጉባዔ ላይ ናቸው፡፡ በኢንዱስትሪ የበለጸጉት ሀገሮች መሪዎቹ አውሮፓ እና መካከለኛው ምስራቅ ውስጥ ጦርነቶች እየተካሄዱ ባሉበት በአሁኑ ወቅት ያለውን የዓለም ጸጥታ ጉዳይ ይወያያሉ፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ እና የቻይና ፉክክርም የጉባዔው ትኩረት እነደሚሆን ተመልክቷል፡፡

መሪዎቹ ቅንጡው ጉባዔው የሚካሄድበት ቅንጡው ቦርጎ ኢኛትዚያ (Borgo Egnatzia) መዝናኛ ሲደርሱ የጣሊያን ጠቅላይ ሚንስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ተቀብለዋቸዋል፡፡ አክራሪ ቀኝ ክንፉ የሜሎኒ ፓርቲ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በተካሄደው የአውሮፓ ፓርላማ ምርጫ 29 ከመቶ ድምጽ ያገኘ ሲሆን ጠንከር ያለ ድጋፍ አግኝተው የወጡ ብቸኛዋ የዋና የምዕራብ አውሮፓ ሀገር መሪ አድርጓቸዋል፡፡

ባይደን በሌላ በኩል በድጋሚ ለመመረጥ የሪፐብሊካን ፓርቲው ዕጩ እንደሚሆኑ ከሚጠበቁት ከቀድሞው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ጋር ብርቱ ፉክክር ላይ ሲሆን በግልም አስቸጋሪ ጉዳይ ገጥሟቸዋል፡፡ በጣሊያኑ ጉባዔ ላይ ለመገኘት ከመነሳታቸው በአንድ ቀን ቀደም ብሎ ማክሰኞ ዕለት ልጃቸው ሀንተር ባይደን የሱስ አስያዥ ቁስ ሱሰኛ ሆነው ሳለ መሣሪያ በመግዛት ወንጀል ክስ ጥፋተኛ ተብለዋል፡፡

ያም ሆኖ ባይደን መሪዎቹን ለዩክሬይን 50 ቢሊዮን ዶላር ብድር እንዲሰጣት ለማግባባት ተስፋ በማድረግ ወደጉባዔው ተጉዘዋል፡፡ የቻይናን የኤሌክትሪክ መኪናዎች ጨምሮ በስትራተጂያዊ የአረንጓዴ ቴክኖሎጂ አቅም ጉዳዮች ስምምነት እንደሚደርግ ተስፋ አድርገው ተጉዘዋል፡፡ የአውሮፓ ህብረት ባይደን ጣሊያን ከመግባታቸው በአንድ ቀን ቀደም ብሎ በቻይና የኤሌክትሪክ መኪናዎች ላይ ቀረጥ በመጣል እንደሚደግፋቸው ፍንጭ ሰጥቷል፡፡

ባይደን በተጨማሪም አፍሪካ ላይ መዋዕለ ነዋይ መመደብ፡ ዓለም አቀፍ ልማት እና የአየር ንብረት ጉዳዮችን ቁልፍ አጀንዳዎቹ ላደረገው የጂዮርጂያ መሎኒ አስተዳደር ፖሊሲ ድጋፋቸውን ገልጠዋል፡፡ በጉዳዮቹ ላይ በዛሬው የጉባዔው መክፈቻ ላይ ውይይት የተደረገበት ሲሆን በማስከተል የጋዛ እና የዩክሬይን ጦርነቶች ላይም ተወያይተዋል፡፡

ቀን አክራሪዋ የጣሊያን ፖለቲከኛ መሎኒ አፍሪካዊያን ፍልሰተኞች በሜዲቴራኒያን ባሕር በኩል ወደ አውሮፓ እንዳይገቡ ለመከላከል በባሕር ኅይል መርከቦች ይታጠር የሚል ጥሪ ማቅረባቸው ሲታወስ በአሁኑ ወቅት ደግሞ አፍሪካ ላይ ዓለም አቀፍ ኢንቬስትመንት በማጠናከር ያንን ግብ ለማሳካት ይፈልጋሉ፡፡

መሎኒ በርካታ የአእፍሪካ መሪዎችን በጉባዔው ላይ በታዛቢነት እንዲገኙ ጋብዘዋል፡፡ ከተጋበዙት መካከል የአልጄሪያ ፕሬዚደንት አብደልመጂድ ቴቡኒ፣ የቱኒዥያው ካይስ ሳኢድ፣ የኬኒያው ዊሊያም ሩቶ እና የሞሪታኒያው መሐመድ ኡልድ ጋዙዋኒ ይገኙባቸዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG