በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን የሰው ሠራሽ አእምሮ ቁጥጥርን የሚያረጋግጥ ፕሬዚዳንታዊ ትዕዛዝ ፈረሙ


የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን
የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ እጅግ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች፣ የሰው ሠራሽ አእምሮን አሠራር እና እድገት አስመልክቶ፣ የብሔራዊ ደኅንነትንና የተገልጋዩን ማኅበረሰብ መብቶች መጠበቅ በሚያረጋግጥ መልኩ ሚዛን ጠብቀው እንዲሠሩ የሚያስገድድ ፕሬዚዳንታዊ ትዕዛዝ፣ ትላንት ሰኞ ፈረሙ።

ዐይነተኛ እንደኾነ የተነገረለት ይኸው ፕሬዚዳንታዊ ትዕዛዝ፣ አገሪቱ በምታወጣቸው ሕጎች እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚደረሱ ስምምነቶች የሚጠናከር ቅድመ ጥበቃ ለማበጀት የታለመ ነው።

ባይደን፣ ፕሬዚዳንታዊውን ትዕዛዝ ከመፈረማቸው አስቀድሞ በሰጡት አስተያየት፣ በቴክኖሎጂው ጎራ የሚታዩትን ለውጦች “በኀያል ቅልጣፌ እና ፍጥነት” እየመራ ያለው የሰው ሠራሽ አእምሮ፣ ከፍተኛ ጠቀሜታ የማስገኘትም ኾነ አደጋ የማስከተል ግዙፍ ዐቅም እንዳለው አመልክተዋል።

“የሰው ሠራሽ አእምሮ በዙሪያችን በምልአት አለ፤” ያሉት ባይደን፣ “ሊያስገኝ የሚችለውን ዕድል እውን ለማድረግና ሊያስከትል የሚችለውንም አደጋ ለማስወገድ፣ ቴክኖሎጂውን በወጉ መቆጣጠር መቻል አለብን፤” ብለዋል።

ውሳኔው፣ ሰው ሠራሽ አእምሮ፥ አሳሳች እና አውዳሚ በመኾን ፈንታ፤ እምነት የሚጣልበትና ጠቃሚ እንዲኾን የሚያግዝ ቀዳሚ ርምጃ እንደኾነ ተመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG