በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አንተኒ ፋውቺን ኮቪድ ያዛቸው


ፎቶ ፋይል፦ ዶክተር አንተኒ ፋውቺ
ፎቶ ፋይል፦ ዶክተር አንተኒ ፋውቺ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት የጤና ጉዳዮች አማካሪ እና በዚህ እና በቀድመው የጸረ ኮቪድ-19 ምላሽ ሚናቸው የሚታወቁት ዶክተር አንተኒ ፋውቺ ኮቪድ-19 እንደያዛቸው ተገለጸ።

የሰማኒያ አንድ ዓመቱ ፋውቺ የኮቪድ መከላከያ ክትባታቸውን ሙሉ በሙሉ ተከትበዋል። አስከትለውም ሁለት ጊዜ ማጠናከሪያ ክትባቶች ወስደዋል። ትናንት ብሄራዊ የጤና ኢንስቲቱት ባወጣው መግለጫ እንዳለው ፋውቺ ያላቸው መለስተኛ የሆነ የኮቪድ ህመም ምልክት ብቻ ነው።

ዶክተር ፋውቺ በቅርብ ቀናት ከፕሬዚዳንት ባይደንም ይሁን ከሌላ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣን ጋር በቅርበት የተገናኙበት አጋጣሚ አልነበረም። ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው በምርመራ ሲረጋገጥ ወደመስሪያ ቤታቸው (ኤን አይ ኤች) ስራቸው እንደሚገቡ መግለጫው አክሎ አስታውቋል።

የፕሬዚዳንት ባይደን አማካሪው ፋውቺ የብሄራዊ የአለርጂ እና የተላላፊ በሽታዎች ተቋም ዋና ዳይሬክተር ናቸው። በቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ አስተዳደር ዘመን የጸረ ኮቪድ-19 ግብረ ኃይል አመራር አባላት አንዱ ነበሩ።

በዚሁ ሳምንት የዩናይትድ ስቴትስ የጤና ሚኒስትር ሃቪየር በሴራ በቫይረሱ እንደተያዙ ተገልጿል።

XS
SM
MD
LG