በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን በፖርተ ሪኮ አውሎ ነፋስ ያደረሰውን ጉዳት ጎበኙ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ ጅል ባይደን
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ ጅል ባይደን

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን “ፊዮና” ተብላ የተሰየመችው አውሎ ንፋስ ከሁለት ሳምንት ነፊት በፖርተ ሪኮ ላይ ያደረሰችውን ጉዳት ትናንት ተገኝተው ተመልክተዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ግዛት የሆነችውን ፖርተ ሪኮ መልሶ ለመገንባት 60 ሚሊዮን ዶላር መንግሥታቸው እንደመደበም ይፋ አድርገዋል።

ከፍተኛ ጉዳት በደረሰባት ፓንስ ከተማ የተገኙት ባይደን አስተዳደራቸው ፖርተ ሪኮን ለመገንባት ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረው ቃል የተገባው “እያንዳንዱ ዶላር መድረሱን” እንደሚያረጋግጡ አስታውቀዋል። “እዚህ በአካል የተገኘነው ከእናንተ ጎን መሆናችንን ለማሳየት ነው፤ ከአደጋው በምታገግሙበትና መልሶ ግንባታ በምታከናውኑበት ወቅት አሜሪካውያን ከጎናችሁ ናቸው። አገረ ገዢ! … እርግጠኛ ነኝ! … እርግጠኛ ነኝ! የምትፈልጉትን ሁሉ ማድረግ እንችላለን። በዚህ ደሴት ጉዳይ ቁርጠኛ ነኝ”

60 ሚሊዮን ዶላሩ ለጎርፍ ግድቦች መሥሪያና የጎርፍ አደጋ ማስጠንቀቂያ ሥርዓትን ለመዘርጋት እንደሚውል ዋይት ሃውስ አስታውቋል።

አውሎ ነፋስ ፊዮና ከሁለት ሳምንት በፊር ፖርተ ሪኮን ስትመታ፣ በደሴቲቱ በአጠቃላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጧል።

የፖርተ ሪኮ ገዢ ፔድሮ ፒርሉሲ ትናንት እንዳስታወቁት 93 በመቶ የሚሆነው የኤሌክቲሪክ ሃይል መልሶ ተቀጥሏል። ደሴቲቱ አምስተኛ ደረጃ ባላትና ማሪያ በተሰኘች አውሎ ነፋስ ከአምስት ዓመት በፊት ከደረሰባት ጉዳት እስከአሁን ሙሉ ለሙሉ አላገገመችም።

ባይደን ከባለቤታቸው ጅል ጋር በመሆን መልሶ ግንባታ ላይ ካሉ ቤተሰቦችና የማኅበረሰብ መሪዎች ጋር ተገናኝተዋል።

ባይደን ዛሬ ባለፈው ሳምንት በአውሎ ነፋስ ጉዳት ወደደረሰባት ፍሎሪዳ አገረ ግዛት እንደሚጓዙ ይጠበቃል።

XS
SM
MD
LG