በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጆ ባይደን የአስተዳደር ርክክብ ዝግጅታቸውን ጀምረዋል


ፎቶ ፋይል፦ ጆ ባይደን እና ካማላ ሃሪስ
ፎቶ ፋይል፦ ጆ ባይደን እና ካማላ ሃሪስ

ረጅም ጊዜ በወሰደውና አነታራኪ በሆነው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሪፖብሊካኑን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕን ማሸነፋቸው የተነገረላቸው ዲሞክራቱ ጆ ባይደን ከወዲሁ የአስተዳደር ርክክብ ዝግጅታቸውን ፈጥነው ጀምረዋል።

በመጪው እአአ ጥር ሃያ ቃለ መሃላ ፈጽመው ሲረከቡ ቁልፍ የሆኑ የትረምፕ ፖሊሲዎችን እንደሚቀለብሱ ተጠቁሟል።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ባይደን በጠባብ አጠቃላይ ድምጽ የመራጭ ተወካይ ድምጾችን ባሰነፉባቸው ክፍለ ግዛቶች የተፈጸሙ የድምጽ ቆጠራ መዛባቶች ሲፈተሹ ውጤቶቹ ተቀልብሰው አሸናፊ እኔ እሆናለሁ በማለት ክሶች መስርተዋል።

ተመራጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና ምክትላቸው ካማላ ሃሪስ ትናንት የሽግግር ዌብሳያታቸውን ከፍተዋል።

አፋጣኝ ትኩረታቸው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ፤ በወረርሽኙ ምክንያት የደቀቀው ኢኮኖሚ የአየር ንብረት ለውጥና የስርዓታዊ ዘረኝነት ጉዳይ እንደሚሆን አሳውቀዋል።

ባይደን በቀድሞ የምግብ እና መድሃኒት አስተዳደር ኮሚሺነር ዶ/ር ዴቪድ ኪስለር እና በዬል ዩኒቨርስቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶ/ር ማርሴላ ኑኔዝ ስሚዝ የሚመራ አስራ ሦስት አባላት ያሉት የኮሮናቫይረስ ምክክር ኮሜቴ አቋቁመዋል።

ፕሬዚዳንት ትረምፕ በምርጫው መሸነፋቸውን ለመቀበልም ሆነ ለጆ ባይደን ቴሌፎን ደውለው ለማነጋገር ፈቃደኛ አልሆኑም።

XS
SM
MD
LG