ከ50 ዓመታት አገልግሎት በኋላ የፖለቲካ ሥልጣናቸውን ያገባደዱት ጆ ባይደን ዋይት ሃውስን ተሰናብተው ፊታቸውን ወደ ግል ህይወታቸው ለማዞር ከቤተሰባቸው ጋራ ወደ ካሊፎርኒያ ቢያቀኑም "የያዝነውን ትግል ግን ቸል ብለን አንተውም” ብለዋል።
ባይደንን የተኩት አዲሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከእርሳቸው በፊት የነበሩት ዲሞክራቱ ፕሬዝዳንት ባይደን ያደረጉትን “ሙሉ በሙሉ እና ጨርሶ ለመቀልበስ” ቃል የገቡበትን የመክፈቻ ንግግራቸውን ከተከታሉ በኋላ ብዙም ሳይቆዩ ተናግረዋል። ባይደን ከአራት ዓመታት በፊት ሥልጣን ላስለቀቋቸው ሰው የአክብሮት አስተያየት ሰንዝረዋል።
እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2020 በተካሄደው ምርጫ መሸነፋቸውን ያላመኑት ትራምፕ በአንጻሩ በ2021 የባይደን በዓለ ሲመት በተካሄደበት ወቅት በወጉ መሠረት ለባይደን ተመሳሳይ መልካም አስተያየት ለመስጠት እና አክብሮት ለማሳየት ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸው ይታወሳል።
መድረክ / ፎረም