በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን ከኬኔዲ ቤተሰብ ድጋፍ አገኙ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን

በመጪው የአሜሪካ ምርጫ ወደ የትኛውም ፓርቲ ልታዘም እንደምትችል በሚነገርላት የፔንሲልቬኒያ ግዛት የሦስት ቀናት ዘመቻ ላይ የሚገኙት ፕሬዚድንት ጆ ባይደን፣ በአሜሪካ በአንጋፋ የፖለቲካ ቤተሰብነት ከሚታወቁት 15 የኬኔዲ ቤተሰብ አባላት ዛሬ በይፋ ድጋፍ እንደሚሰጣቸው በመጠበቅ ላይ ነው።

አንዱ የቤተሰብ አባል የሆኑት ሮበርት ኤፍ ኬኔዲ ትንሹ፣ በግል ለመወዳደርና የዲሞክራቲክ ፓርቲውን ለመገዳደር መወሰናቸውን ተከትሎ፣ ከቤተሰብ አባሎቻቸው ውግዘት ተከትሏል።

የባይደን የምርጫ ዘመቻ ቡድን ከኬኔዲ ቤተሰብ አባላት ድጋፍ ለመቀበል መወሰኑ፣ የግል ተወዳዳሪው ትንሹ ኬኔዲ የቤተሰባቸውን መልካም ዝና በመጠቀም የባይደንን ድጋፍ ሊሸረሽሩ ይችላሉ የሚለውን ስጋት ከምር መያዙን ያመለክታል ተብሏል።

ትንሹ ኬኔዲ በማኅበራዊ ሚዲያ ባሠፈሩት መልዕክት፣ ቤተሰቦቻቸው በፖለቲካ አመለካከት ቢለያይም፣ አንዳቸው ለሌላው ያላቸው ፍቅር ግን የፀና መሆኑን አመልክተዋል።

የቀድሞው ፕሬዚደንት ጃን ኤፍ ኬኔዲ የወንድም ልጅ የሆኑትና፣ በግል ለሚወዳደሩት ኬኔዲ ትንሹ ደግሙ እህት የሆኑት ኬሪ ኬኔዲ፣ ቤተሰባቸው ለጆ ባይደን ያለውን ድጋፍ ዛሬ በይፋ እንደሚያሳውቁ የባይደን የምርጫ ዘመቻ ቡድን አስታውቋል።

ባለፈው መጋቢት በተከበረው የቅዱስ ፓትሪክ ቀን፣ 30 የሚሆኑና የዲሞክራሲያዊ ፓርቲውን መሥመር አጠንክረው የሚከተሉትን የኬኔዲ ቤተሰብ ዓባላትን፣ ፕሬዝደንት ባይደን በዋይት ሃውስ ተቀብለው አስተናግደዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG