በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን በነጻነት ቀን በዓሉ ተስፋን ማሳደር ፈልገዋል


ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና ባለቤታቸው ጂል ባይደን ትናንት ሰኞ ተከብሮ የዋለው “ፎርዝ ኦፍ ጁላይ” ንግግር ሲያደርጉ፤ ዋይት ኃውስ እአአ ጁላይ 4/2022
ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና ባለቤታቸው ጂል ባይደን ትናንት ሰኞ ተከብሮ የዋለው “ፎርዝ ኦፍ ጁላይ” ንግግር ሲያደርጉ፤ ዋይት ኃውስ እአአ ጁላይ 4/2022

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና ባለቤታቸው ጂል ባይደን ትናንት ሰኞ ተከብሮ የዋለውና “ፎርዝ ኦፍ ጁላይ” ተብሎ የሚጠራው የዩናይትድ ስቴትስ የነጻነት ቀንን አስመልከቶ ተስፋ ሰጭና የአንድነት ጥሪ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ይህ የሆነው 85 ከመቶ የሚሆኑት አሜሪካውያን አገሪቱ የምትጓዝበት አቅጣጫ የተሳሳተ መሆኑን በተሰበሰበው የህዝብ አስተያየት ድምጽ በገለጹበትና የፖለቲካ ጽንፈኝነት ዋነኛው አሳሳቢ ጉዳይ በሆነበት ወቅት መሆኑ ተመልክቷል፡፡

“አሜሪካ ሁልጊዜ በእንቅስቃሴ ላይ ነች ሁል ጊዜም በመሻሻል ሥራ ላይ ነች፣” በማለት ባይደን ከባለቤታቸው፣ በመቶዎች ከሚቆጠሩ የሠራዊቱ አባላት ቤተሰቦችና ከአስተዳደሩ ሠራተኞች ጋር በመሆን በዋይት ኃውስ ጊቢ መስክ ላይ በተሰናዳ ግብዣ በዓሉን ባከበሩበት ወቅት ተናግረዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ አያይዘውም“ መሻሻል፣ ሁሉ ጊዜም በእንቅስቃሴ ላይ ተስፋን መሰነቅና ቃል ኪዳንን ማሟላት” የሚል አስተያየት አክለዋል፡፡

አሜሪካውያን ያሉበትን ሁኔታ ያልዘነጉ መሆኑን የገለጹት ባይደን መልካሞቹ ብሩህ ቀናት ወደፊት መሆናቸውን በመግለጽ “ምጣኔ ሀብታችን እያደገ ነው፣ ይሁን እንጂ ያለ ምንም ህመም ግን አይደለም” ብለዋል፡፡

በዋይት ኃውስ የተከበረው የነጻነት ቀን እአአ ከ2019 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰዎች በአካል የተገኙበት የኒው ዮርኩን ጨምሮ በበርካታዎቹ የአገሪቱ ክፍሎች ተከብሮ መዋሉ ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG