በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን: በሐማስ ጥቃት ዩናይትድ ስቴትስ አስቸኳይ ርምጃ እንድትወስድ ም/ቤቱን ጠየቁ


ባይደን: በሐማስ ጥቃት ዩናይትድ ስቴትስ አስቸኳይ ርምጃ እንድትወስድ ም/ቤቱን ጠየቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:59 0:00

ባይደን: በሐማስ ጥቃት ዩናይትድ ስቴትስ አስቸኳይ ርምጃ እንድትወስድ ም/ቤቱን ጠየቁ

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ በትላንትናው ዕለት ባሰሙት ንግግር፣ የሐማስ ታጣቂዎች በእስራኤል ላይ የሰነዘሩትን ድንገተኛ ማጥቃት ተከትሎ በተፋፋመው ውጊያ፣ ‘ከእስራኤል ጎን እንደሚቆሙና እስራኤልን እንደሚደግፉ’ ገልጸዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ላይ፣ በእስራኤል ወገን እስከ አሁን የታወቁትን 14 አሜሪካውያን ጨምሮ ከአንድ ሺሕ በላይ ሰዎች እንደተገደሉ ታውቋል፡፡ በዚኽም፣ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ የገባውን የመካከለኛው ምሥራቅ ኹኔታ ለማርገብ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አስቸኳይ ርምጃ እንዲወስድ እጠይቃለኹ፤ ብለዋል።

ጉዳዩን በቅርበት እንደሚከታተሉ ተንታኞች አስተያየት፣ በሐማስ ታጣቂ ኃይሎች ታግተው የተወሰዱ አሜሪካውያን መኖራቸውም፣ የጦርነቱን ይዞታ ይበልጥ አወሳስቦታል።

የአሜሪካ ድምጿ አኒታ ፓውል ከኋይት ሃውስ ያጠናቀረችው ዘገባ ዝርዝሩን ይዟል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG