በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚዳንት ባይደን “የአገሬው ሰዎች"ን "ቀን” አወጁ


"የአገሬው ሰዎች" እኤአ ጥቅምት 8 2017 ኒዮርክ ላይ በተደረገው አቀፍ የአገሬው ሰዎች ቀን” በዓል ላይ፡፡ በዓሉ የተካሄደው ኮሎምቦስ ዴይ እየተባለ የሚከበረውን በዓል በመቃወም ነው፡፡
"የአገሬው ሰዎች" እኤአ ጥቅምት 8 2017 ኒዮርክ ላይ በተደረገው አቀፍ የአገሬው ሰዎች ቀን” በዓል ላይ፡፡ በዓሉ የተካሄደው ኮሎምቦስ ዴይ እየተባለ የሚከበረውን በዓል በመቃወም ነው፡፡

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በአገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ (ቀደምቶቹ) “የአገሬው ሰዎች ቀን” (Indigenous Peoples Day) የሚል ፕሬዚዳንታዊ አዋጅ በትናንትናው እለት አውጥተዋል፡፡

አዋጁ እስከዛሬ በፌደራል ደረጃ “የክርስቶፈር ኮሎምበስ ቀን” በሚል የሚከበረውን በዓል የአገሬው ሰዎች ይበልጥ ወደ ሚታሰቡበትና የሚከበሩበት እለት ለመቀየር ፣ የሚደረገውን ጥረት ያበረታታል ተብሏል፡፡

ባይደን የፊታችን ሰኞ ጥቅምት 1 የሚከበረውና በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የተወሰነው የኮሎምበስ ቀንም እንዲሁ ተያይዞ እንዲከበር አውጀዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ አዋጁ “የአገሬው ሰዎች ጽናትና ጥንካሬ፣ እንዲሁም በያንዳንዱ የአሜሪካ ማህበረሰብ ገጽታ ላይ፣ ያደረጉትን የማይለካ በጎ አስተዋጾ ለማስታወስ ነው” ብለዋል፡፡

“ኔቲቭ አሜሪካን” በመባል የሚታወቁት ቀደምቶቹና ነባሮቹ አገሬዎች፣ የአገሪቱን ተወላጆች የሚያስብ እለት እንዲሰየም፣ ለረጅም ጊዜ ሲታገሉ መቆየታቸው ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG