በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፕሬዚዳንት ባይደን ውሳኔዎችና ረቂቁ የስደተኞች ህግ ምን ይዟል?


የህግ ጠበቃ ሙሉእመቤት አለማየሁ እና የህግ ጠበቃ የሚ ጌታቸው
የህግ ጠበቃ ሙሉእመቤት አለማየሁ እና የህግ ጠበቃ የሚ ጌታቸው

ፕሬዚዳንት ባይደን ሥልጣን በያዙ የመጀመሪያው ቀን የስደተኞች ህግን አስመልከቶ እጅግ ወሳኝ ናቸው የሚባሉ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ለአፈጻጸማቸውም ትእዛዝትን ሰጥተዋል፡፡

እንዲሻሻል በሚፈልጉት የስደተኞች ህግ ውስጥ የሚካተተውን አዲስ የዜግነት ረቂቅ ህግም ይፋ አድርገዋል፡፡

በእነዚህና በሌሎች የስደተኞች ህግ ጉዳዮች ዙሪያ፣ በካሊፎርኒያ ሳንሆዜ የህግ ጠበቃ የምስራች ጌታቸውና፣ እንዲሁም በካሊፎርኒያ ሎስ አንጀለስ የህግ ጠበቃ ሙሉእመቤት አለማየሁ ማብራሪያ ይሰጡናል፡፡

በዚህ ውይይት የህግ ባላሙያና ጠበቆቹ በቀረበው ረቂቅ የዜግነት ህግ እና ፖሊሲዎችም ዙሪያ ያብራሯቸው ሌሎች ጉዳዮችም አሉ፡፡

የፕሬዚዳንት ባይደን ውሳኔዎችና ረቂቁ የስደተኞች ህግ ምን ይዟል?
please wait

No media source currently available

0:00 0:28:57 0:00

ከእነዚህ መካከል ለምሳሌ

  • የዲቪ ሎቶሪ ፕሮግራም እንዲቀጥል፡፡ እንዲያውም በተጨማሪም በየዓመቱ የሚፈቀደው የቪዛ መጠን ከ55ሺህ ወደ 80ሺህ ከፍ እንዲል ስለመጠየቁ፣
  • ከጃኑዋሪ 20/2017 በኋላ ከአገር ለቀው እንዲወጡ ውሳኔ የተላለፈባቸው ሰዎችን በተመለከተ፣
  • በቤተሰብና ዝምድና ላይ የተመሰረቱ የኢምግሬሽን ጉዳዮችን በተመለከተ የቀረቡ ማሻሻያዎች፣
  • ቋሚ መኖሪያ ጥያቄን አስመልክቶ ስለተነሱ ገደቦች፣
  • በስራ ቅጥር ስለሚሰጡ ቪዛዎች፣
  • በኢምግሬሽን ፍርድ ቤቶች ስለተከማቹ ጉዳዮችና እንዲሁም ደግሞ ባለጉዳይ ስደተኞች በእነዚህ ሁሉ መካከል ምን ዝግጅቶችን ማድረግ እንደሚኖርባቸው ባለሙያዎቹ የሰጡንን ማብራሪያ ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG