በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን ወደ አውሮፓ አቀኑ


ዩናይድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፤ ቀዳማዊት ዕመቤት ጂል ባይደን
ዩናይድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፤ ቀዳማዊት ዕመቤት ጂል ባይደን

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከበለጸጉ አገራት መሪዎች ለመገናኘትና ከትልቅ የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ዛሬ ወደ አውሮፓ አምርተዋል፡፡

ባይደን መጀመሪያ ወደ ሮም በማቅናት ከነገ በስቲያ ጀምሮ ጥቅምት 20 እና 21 በሚካሄደው የቡድን 20 አባል አገሮች የመሪዎች ጉባኤ ላይ ይሳተፋሉ፡፡

በዚህ ጉባኤ የባለጸጋዎቹ አገራት መሪዎች ስለ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ፣ ስለ አየር ንብረት ለውጥ የዓለም የምጣኔ ሀብት ማንቀሳቀስ ስለሚቻልበት ሁኔታ ይወያያሉ፡፡

ከዚያም በመቀጠል፣ ወደ ስኮትላንድ ግላስኮ በመሄድ ከጥቅምት 21 ጀምሮ በሚካሄደው የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ ይገኛሉ፡፡

ከዚያ በፊት በጣልያን ቆይታቸው፣ ባይደን ራሳቸው አማኝ ከሆኑበት ቤተክርስቲያን፣ የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ጋር ይገናኛሉ፡፡

የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ጄክ ሱሊቨን በዚህ ሳምንት ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ስብሰባውን የሚመሩት ፕሬዚዳንት ባይደን ናቸው፡፡

የቻይናው ፕሬዚዳንት ዚ ጂንፒንግም ሆነ የሩሲያው መሪ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑትን በሁለቱም ስብሰባዎች በአካል አይገኙም፡፡

በቡድን 20 አባል አገራቱም ሆነ በአየር ንብረት ለውጡ ጉባኤ የሚገኙት አውሮፓውያንና አሜሪካውያን የታላላቆቹን ጉዳዮች አጀንዳ በመቅረጽ በጋራ እንደሚሰሩ አማካሪው ተናግረዋል፡፡

በዓለም አቀፎቹ መድረኮች ሌሎች በርካታ ወቅታዊና አሳሳቢ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች እንደሚነሱም ይጠበቃል፡

XS
SM
MD
LG