በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን ፈረንሣይ ይገኛሉ


ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ኦርሊ አውሮፕላን ማረፊያ ፓሪስ፣ ፈረንሣይ እአአ ሰኔ 5/2024
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ኦርሊ አውሮፕላን ማረፊያ ፓሪስ፣ ፈረንሣይ እአአ ሰኔ 5/2024

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የተባበሩት ኃይሎች ኖርማንዲ፣ ፈረንሣይ የገቡበት 80ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ ለመገኘት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ፓሪስ ገብተዋል።

የፕሬዝደንቱ ጉብኝት፣ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ወረራ በፈጽመችበት በዚህ ወቅት፣ ጠንካራ የሆነ አትላንቲክን ተሻጋሪ ግንኙነት አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ለመስጠት ያለመም ነው ተብሏል።

ባይደን በተደጋጋሚ ፈረንሣይን ከጠንካራ የአሜሪካ አጋሮች እንዷ እንደሆነች ሲገልጹ ቆይተዋል። ከሁለት ዓመታት በፊት አስተዳደራቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ኦፊሴላዊ ጉብኝት በአሜሪካ እንዲያደርግ የጋበዘው የፈረንሣይን መሪ ነበር።

ባይደን በተጨማሪም የሁለተኛውን የዓለም ጦርነት በድል ለማጠናቀቅ ወሳኝ የሆነውን የኖርማንዲ ጦርነት ለማሰብ በተዘጋጀው ሥነ ስርዓት ላይ ከተጋበዙት የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዜሌኒስኪ ጋራ እንደሚገናኙ ይጠበቃል።

ባይደን ለጋዛው ጦርነት የሚሰጡት ድጋፍ የገጠመው ተቃውሞ፣ ለዩክሬን ድጋፍ ለማሰባሰብ በሚያደርጉት ጥረት ላይ እንቅፋት እንደሆነ ተንታኞች በመናገር ላይ ናቸው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG