የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ዋይት ሃውስ እንደገቡ ቅድሚያ ከሰጧቸው ጉዳዮች አንዱ የሃገራቸው ዓለምአቀፍ ግንኙነት ነው።
ፕሬዚዳንቱ ሃገራቸውን ወደ ፓሪስ የአየር ንብረት ስምምነትና ወደ ዓለም የጤና ድርጅት አባልነት መልሰዋል።
የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱን ሠራተኞች ሰብስበው ሲናገሩ “አሜሪካ ተመልሳለች”፣ “ዲፕሎማሲ ተመልሷል” ብለዋል ለሃገራቸውም ለዓለምም በቀጥታ በተሠራጨ ፕሮግራም።
ለአፍሪካ ኅብረት 34ኛ የመሪዎች ጉባዔ መክፈቻ በቪድዮ ቀርፀው በላኩት ንግግር እጅግ ወዳጃዊ መልዕክት አስተላልፈዋል። “ፈተናዎቻችንን የመጋፈጥ አቅም አለን፤ አሜሪካ አብራችሁ አለች” ብለዋል።
ይህ የባይደን ፖሊሲ ለዓለም ምን ትርጉም ይኖረው ይሆን?
በሰሜን ካሮላይና ኤ ኤንድ ቲ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና የዓለምአቀፍ ግንኙነቶች፣ እንዲሁም አቴንስ ኦሃዮ በሚገኘው ስክሪፕስ የጋዜጠኛነት ትምህርት ቤት የጋዜጠኛነት መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር ቡሩክ ኃይሉ ትንታኔና ማብራሪያ ይሰጡናል። ፕሮፌሰር ቡሩክ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፖሊቲካል ሳይንስ አስተምረዋል። በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት /ዩኔስኮ/ የኢትዮጵያ ተጠሪ ሆነው አገልግለዋል። በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ ምክትል አምባሳደርነት ድረስ ሠርተዋል። አሁን በሰሜን ካሮላይና የኢትዮጵያ የክብር ቆንሲል ሲሆኑ የኢትዮጵያ አሜሪካ ሲቪክ ምክር ቤትና የመማክርት መረብ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና ዋና ዲፕሎማቲክ አማካሪ፣ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ግንኙነት ጥምረት የሥራ አስፈፃሚ አባል እንዲሁም የሌሎችም ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊያንን የሚመለከቱ ተሟጋችና ሲቪክ ቡድኖች አማካሪና አስተባባሪም ሆነው ያገለግላሉ።
ሙሉውን ትንታኔ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።