በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን "ምዕራቡ ዩክሬንን አይተዋትም" አሉ


የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የተባበሩት ኃይሎች ኖርማንዲ፣ ፈረንሣይ የገቡበትን 80ኛ ዓመት ክብረ በዓል (D-day) ለማክበር በፓሪስ
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የተባበሩት ኃይሎች ኖርማንዲ፣ ፈረንሣይ የገቡበትን 80ኛ ዓመት ክብረ በዓል (D-day) ለማክበር በፓሪስ

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ዩናይትድ ስቴትስ እና ኔቶ ዩክሬንን ለሁለት ዓመታት የፈጀውን ወረራ በመቃወም ለዩክሬን የሚሰጡትን ድጋፍ እንደማይተዉ ዛሬ ሀሙስ ተናገሩ፡፡

ባይደን ይህን የተናገሩት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የተባበሩት ኃይሎች ኖርማንዲ፣ ፈረንሣይ የገቡበትን 80ኛ ዓመት ክብረ በዓል (D-day) ለማክበር ዛሬ ፓሪስ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር ነው፡፡

“ለዩክሬን ከምንስጠው ድጋፍ ወደ ኋላ አንልም፣ ለሚያስፈራሩትም አንንበረከክም” ያሉት ባይደን ፣ እንደ ሩሲያው ፕሬዝዳንት ፑቲን ላሉ "ጉልበተኞች እጅ መስጠት፣ ለአምባገነኖች መገዛት በቀላሉ የማይታሰብ ነገር ነው" ሲሉ በኖርማንዲ የአሜሪካ መቃብር ስነ ስርዓት ላይ ተናግረዋል።

"ይህን ብናደርግ በእነዚህ የተቀደሱ የባህር ዳርቻዎች ላይ የተከሰተውን ነገር እንረሳለን ማለት ነው." ሲሉም ፕሬዚዳንቱ አክለዋል፡፡

“ዩክሬን የተወረረችው በሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ነው፣ ያሉት ባይደን “የበላይነትን የሚሹ አምባገነን” ናቸው ብለዋቸዋል፡፡

ዴሞክራሲ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ አሁን ከየትኛውም ጊዜ በላይ አደጋ ላይ ወድቋል” ሲሉም ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል።

ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የተፈጠረውን ዓለም አቀፋዊ ትብብር አስፈላጊነት በማጉላት ዕለቱ (D-day) “ሀገራትን የበለጠ ጠንካራ እንደሚያደርጋቸው የሚያሳይ ጠንካራ ምሳሌ ነው” ብለውታል።

ይህ የባይደን ንግግር የተሰማው ከአምስት ዓመት በፊት በ75ኛው ተመሳሳይ ክብረ በዓል ላይ ተገኝተው ንግግር ካደረጉት ከሪፐብሊካኑ ተፎካካሪያቸው የቀደሞ ፕሬዝዳንት ትረምፕ ጋር ፣ በድጋሚ ለመመረጥ በሚያደርጉት የ2024 የምርጫ ዘመቻ ወቅት ነው፡፡

የምዕራቡ ዓለም ዋና ወታደራዊ ጥምረት ስለሆነው ኔቶ አስፈላጊነትና የዩናይትድ ስቴትስ ቁርጠኝነት ብዙ ጊዜ ጥያቄ ያነሱት ትረምፕ፣ በ2019 ንግግራቸው በኖርማንዲ የባህር ዳርቻዎች ጀብድ የፈጸሙ ወታደሮችን ያወደሱ ቢሆንም፣ ከጦርነቱ በኋላ የተፈጠረውን ዓለም አቀፍ ጥምረት አላሞገሱም።

ትረምፕ ብዙ ጊዜ፣ ከሀገራዊ ኢኮኖሚ አጠቃላይ ምርታቸው አንጻር፣ ለሀገራቸው የሚመድቡትን 2 ከመቶ የሚሆነውን የመከላከያ ወጭ ያህል እንኳ ለቃል ኪዳን ህብረቱ አይከፍሉም የሚሏቸውን የአውሮፓ የኔቶ አባላትን ይተቻሉ፡፡

ባይደን ትረምፕ እንደገና ከተመረጡ የአሜሪካ አጋሮችን እንደሚተዉ እና ከኔቶ ሊወጡ እንደሚችሉ በመግለጽ አስተዳደራቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለመፍጠር የሚያደርገውን ጥረት ጠቁመዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG