በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን ሩሲያ ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ሥርዓት እንድትታገድ አደረጉ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በምስራቅ ዩክሬን የሚገኙት ዶኔትሰክ እና ሎውኒስክ ከተሞች ነፃ ሀገራት ለመሆናቸው እውቅና መስጠታቸው ዓለም አቀፍን ህግ የጣሰ ነው በማለት፣ የሩሲያን መንግሥት ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ሥርዓት እንዲታገድና በሁለት ትልልቅ ባንኮች ላይ ማዕቀብ እንዲጣል አድርገዋል።

ባይደን ትናንት ከዋይት ኃውስ በሰጡት አጭር መግለጫ ፑቲን ወታደሮቹን ወደ ምስራቅ ዩክሬን ከተሞቹ መላካቸው ሩሲያ ዩክሬንን የመውረሯ ጅማሮ መሆኑን እንደሚያሳይ ገልፀዋል።

"ፑቲን የጎረቤቱ ሀገር ግዛት ውስጥ የሚገኝ ስፍራን አዲስ ሀገራት ብሎ እንዲያውጅ ማን መብት ሰጠው" ሲሉም ጠይቀዋል።

በተጨማሪም ባይደን በተለያዩ የአውሮፓ አካባቢዎች የሚገኙ የእግረኛ ጦሮች እና የአየር ተዋጊዎች ወደ ራሽያ ድምበር እንዲጠጉ ያዘዙ ሲሆን ተጨማሪ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች በባልቲክስ መሰማራታቸውንና ይህም ዩናይትድ ስቴትስ እና አጋሮቿ የኔቶ አባል ሀገራትን ግዛት እንደሚያስጠብቁ የማያወላዳ መልዕክት ያስተላልፋል ብለዋል።

XS
SM
MD
LG