በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን የ2ሺሕ 500 እስረኞችን ቅጣት አቀለሉ


ተሰናባቹ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን
ተሰናባቹ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን

ተሰናባቹ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ከአደንዛዥ ዕጽ ጋራ በተያያዘ በእስር ላይ የሚገኙ የ2ሺሕ 500 እስረኞች ቅጣት እንዲቀልላቸው ዛሬ ዓርብ ወስነዋል። ቅጣቱ እንዲቀልላቸው የተወሰነላቸው ግለሰቦች ሁከት አልባ በሆነ መንገድ ነገር ግን ከአድንዛዥ ዕጽ ዝውውር ጋራ በተያያዘ ጥፋተኛ ተብለው በእስር ላይ የሚገኙ እንደነበር ተጠቁሟል። የዛሬውን ጨምሮ በጠቃላይ ባይደን በሥልጣን ዘመናቸው ምህረትና የቅጣት ማቅለያ ያደረጉላቸው ሰዎች ቁጥር ከማንኛውም ፕሬዝደት ከፍተኛው እነደሆነ ታውቋል።

ባይደን እንዳስታወቁት የቅጣት ማቅለያው የተደረገላቸው ግለሰቦች በአሁኑ ግዜ ባለው ሕግ ቢዳኙ ኖሮ ቅጣቱ ዝቅተኛ ይሆንላቸው ነበር። ተጨማሪ እስረኞችም የቅጣት ማቅለያ ሊደረግላቸው እንደሚችል ባይደን ጠቁመዋል። ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ስልጣኑን እስከሚረኩቡ ድረስ ባለው ጊዜ ሌሎች ምህረቶችንንና የቅጣት ማቅለያዎችን እንደሚመለከቱም አስታውቀዋል። ይህም በትረምፕ አስተዳደር ኢላማ ሊሆኑ ይችላሉ የሚል ስጋት ላለባቸው ባለሥልጣናትና አጋሮች ቀድመው ምህረት ማድረግን ሊጨምር እንደሚችል ተገምቷል።

ባይደን ባለፈው ወር 1ሺሕ 500 ለሚሆኑ እስረኞች የቅጣት ማቅለያ ያደረጉ ሲሆን፣ ለ39 ደግሞ ምህረት አድርገዋል። ይህም በታሪክ በአንድ ቀን ውስጥ የተሰጠ ከፍተኛው ምህረት ነው ተብሏል። በተጨማሪም በፌዴራል ደረጃ የሞት ቅጣት ከሚጠብቃቸው 40 ግለሰቦች መካከል ለሰላሳ ሰባቱ ወደ ዕድሜ ልክ እስራት እንዲቀየርላቸው አድርገዋል።

ባይደን በተጨማሪም ከጦር መሣሪያና ከግብር ጋራ በተያያዘ ጥፋተኛ ለተባሉት ለልጃቸው ሃንተር ባይደን በቅርቡ ምህረት አድርገዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG