በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን ካናዳን በመጎብኘት ላይ ናቸው


የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃስቲን ትሩዶ
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃስቲን ትሩዶ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንና ቀዳማዊ እመቤት ጂል ባይደን በካናዳ ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ ትናንት አትዋ ገብተዋል።

ሁለቱ ወገኖች ካናዳ የሰሜን አሜሪካ ኤሮስፔስ መከላከያ ዕዝን የምታሻሽልበትን ግዜ በተመለከተና እንዲሁም ስደተኞችን በተመለከተ ሥምምነት ያደርጋሉ ሲሉ አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የካናዳ ባለስልጣን ለአሶሶዬትድ ፕረስ አስታውቀዋል።

ዓለም አቀፍ የሆኑ ጉዳዮችን በተመለከተ ደግሞ፣ በዩክሬን እየተካሄደ ያለው ጦርነት፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ ቻይና እና ዓለም አቀፍ የንግድ ጉዳዮች ላይ ይነጋገራሉ ተብሏል።

የባይደን አስተዳድሰር ከካናዳ ጋር ላላው ግንኙነት ባለፉት 2 ዓመታት ቅድሚያ የሰጠው ጉዳይ ነው ተብሏል።

በሺህዎች የሚቆጠሩ ጥገኝነት ጠያቂ ስደተኞች ከአሜሪካ ወደ ካናዳ የሚገቡበትን ሁኔታ ለማስቆምም እንደሚነጋገሩ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉት የካናዳው ባለሥልጣን ለአሶሶዬትድ ፕረስ አስታውቀዋል።

XS
SM
MD
LG