በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ 5መቶ ሚሊዮን የኮቪድ-19 ክትባት ለታዳጊ ሀገሮች ልትገዛ ነው


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የኢንተርኔት አማካይነት ጉባኤ ሲሳተፉ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የኢንተርኔት አማካይነት ጉባኤ ሲሳተፉ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እአአ 2022 ለታዳጊ ሀገሮች የሚውል 500 ሚሊዮን ተጨማሪ የኮቪድ-19 ክትባት ዩናይትድ ስቴትስ እንደምትገዛ በዛሬው ዕለት አስታውቀዋል።

ከአሁን ቀደምም ዩናይትድ ስቴትስ በፋይዘር እና ባዮንቴክ የተሰሩ አምስት መቶ ሚሊዮን ነጠላ የኮሮናቫይረስ ክትባቶችን እስከ መጭው ዓመት ሰኔ ወር ባለው ጊዜ እንደምትሰጥ ቃል የገባች ሲሆን ፕሬዚዳንቱ ዛሬ ይፋ ከሚያደርጉት ጋር በጠቅላላው አንድ ቢሊዮን ክትባት ይሆናል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ዛሬ አስቀድመው በትዊተር ባወጡት ቃል "አንድ አሜሪካዊ አንድ ክትባት ስንከትብ ሦስት ክትባት ለዓለም ሀገሮች እንለግሳለን"

ፕሬዚደንቱ ከፋይዘር ኩባኒያ የሚገዛውን የተጨማሪውን የኮቪድ ክትባት ልግስና ዛሬ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ጎን በኢንተርኔት አማካይነት ጉባኤ ገልጿል።

ፕሬዚዳንት ባይደን ትናንት በመንግሥታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ባደረጉት ንግግር ዩናይትድ ስቴትስ እስካሁን ለአንድ መቶ የዓለም ሃገሮች 160 ሚሊዮን ክትባት መስጠቷን እና ይህም በማናቸውም ሃገር ከተሰጠው የበለጠ መሆኑን አውስተዋል።

XS
SM
MD
LG