ዋሺንግተን ዲሲ —
ጄኔቫ በሚገኝ የስዊስ ቪላ ውስጥ ያደረጉትን በዲፕሎማሲያዊ ወግ የተካሄደውንና ከፍ ያለ ስፍራ የተሰጠውን ቆይታቸውን ፕሬዝዳንት ባይደን “የውይይታችን ሙሉ መንፈስ .. በአጠቃላይ ለአራት ሰዓታት የዘለቀ ቆይታ እንደነበረ እገምታለሁ .. መልካም፡ አዎንታ የተንጸባረቀበት ነበር።” ብለውታል።
የሩሲያ አቻቸው ቭላድሚር ፑቲንም የባይደንን ግምገማ የተጋሩበትን ሃሳብ “ውይይቱ ፍጹም ገንቢ ነበር” በሚል ነው ገለጡት፡፡
ሁለቱ ወገኖች በእንግሊዝኛው አጠራር 'Strategic stability' በመባል በሚታወቀው እና ሁለቱ አገሮች የኒዩክሌር ጦር መሳሪያ አያያዝን አስመልክቶ ወደ ጥፋት ሊወስድ የሚችል አካሄድን ለመከላከል እና አንዳቸው በሌላው ላይ ሊወስዱ በሚችሉት እርምጃ ሊመጣ የሚችል አደጋን ለማስቀረት በተወጠነው .. ረዥም ዕድሜ ባስቆጠረው ጽንሰ ሃሳብ እና እንዲሁም የሳይበር ደህንነትን በሚመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ለመጀመር ተስማምተዋል።
ሙሉ ዘገባውን ከዚህ ያድምጡ።