በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን ወደ አፍሪካ ሊጓዙ ነው


የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን
የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ለረጅም ግዜ ሲጠበቅ የነበረውን የአፍሪካ ጉብኝት በመጪው ጥር ወር ላይ በአንጎላ እንደሚያደርጉ ዋይት ሃውስ ትላንት ማክሰኞ አስታውቋል።

ባይደን ከሁለት ዓመታት በፊት የአፍሪካ መሪዎችን ዋሽንግተን ላይ ለጉባኤ በጋበዙበት ወቅት አህጉሪቱን እንደሚጎበኙ ቃል ገብተው ነበር።

ጉብኝቱ የአሜሪካ ባላንጣዋ ቻይና በአህጉሪቱ ላይ ያላትን እያደገ የመጣ ተጽእኖ ለመገዳደር አስተዳደሩ የሚያደርገው ጥረት አካል እንደሆነ የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል።

ምክትል ፕሬዝደንት ካመላ ሄሪስን እና ቀዳማዊ እመቤት ጂል ባይደንን ጨምሮ በርካታ የካቢኔ አባላት ባለፈው የፈረንጆች ዓመት በአፍሪካ ጉብኝት አድርገዋል።

የስልጣን ዘመናቸው ጥቂት ወራት የቀሩት ባይደን፣ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በመጪው ጥር 10 እስከ 15 ድረስ በበርሊን፣ ጀርመን እንዲሁም በሉዋንዳ፣ አንጎላ ጉብኝት እንደሚያደርጉ የዋይት ሃውስ የፕሬስ ኃላፊ ካሪን ዣን ፒየር ባይደን ትላንት ኒው ዮርክ በተመድ ጉባኤ ላይ ንግግር ለማድረግ በተገኙበት ወቅት አስታውቀዋል።

ከእ.አ.አ 2015 ወዲህ ከሰሃራ በታች ባሉ ሃገራት አንድ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጉብኝት ሲያደርግ ባይደን የመጀመሪያው ይሆናሉ።

ባይደን በጀርመኑ ጉብኝታቸው፣ ዩክሬን የሩሲያን ወረራ ለመመከት በምታደርገው ጥረት ጀርምመን የምታደርገውን ድጋፍ በተመለከተ ምስጋናቸውን እንደሚገልጹና የአሜሪካንን አጋርነትንም እንደሚያጠናክሩ ታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG