በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የባይደን ከፍተኛ የሳይንስ አማካሪ ሥራቸውን ለቀቁ


ፎቶ ፋይል፦ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፖሊሲ ፅህፈት ቤት ድሬክተር የነበሩት ኤሪክ ላንደር
ፎቶ ፋይል፦ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፖሊሲ ፅህፈት ቤት ድሬክተር የነበሩት ኤሪክ ላንደር

የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከፍተኛ የሳይንስ አማካሪ በሠራተኞቻቸው ላይ አሳይተዋል በተባለው ክብራቸውን ዝቅ የማድረግ ያለተገባ አቀራረብ የቀረበባቸውን ቅሬታ ተከትሎ በትናንትናው ዕለት ሥራቸውን ለቀቁ።

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፖሊሲ ፅህፈት ቤት ድሬክተር የነበሩት ኤሪክ ላንደር የበታች ሠራተኞቻቸው አሳይተዋል ያሉትን አያያዝ የተመለከተ ቅሬታ የውስጥ ግምገማ ትኩረት ሆኖ ነበር።

የተባለው ግምገማ በትናንትናው ዕለት በመጀመሪያ "ፖለቲኮ" በተባለው ጋዜጣ ላይ ዘገባ የቀረበበት ሲሆን፤ ቆይቶም የዋይት ኃውሷ የፕሬስ ጽ/ቤት ኃላፊ ጄንሳኪ ትክክለኝነቱን አረጋግጠው ተናግረው ነበር።

ላንደር ለባይደን ባቀረቡት የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ

"ከዚህ በፊት አብረውኝ የሰሩትንም ሆነ አሁንም ያሉ የሥራ ባልደረቦቼን በማነጋግርበት ወቅት ባደረስኩባቸው ጉዳት በእጅጉ አዝኛለሁ። ተፀጽቻለሁ” ነበር ያሉት።

አንዳንድ ጊዜ "የሚፈታተን እና ትችት" ባዘለ አቀራረባቸው ራሳቸውንም ባልደረቦቻቸውንም ለመገፋፋት ይጥሩ እንደነበር በመጥቀስ "የተናገርኳቸው ነገሮች እና የተናገርኩባቸው መንገዶች አንዳንድ ጊዜ ከተገቢው መስመር ያለፉ እና የሌሎችን ክብር ያጎደሉ ነበሩ" ሲሉ ቅሬታዎቹን አምነው ተቀብለዋል።

በላንደር ላይ የቀረቡት ውንጀላዎች የአንዳንዶችን ሥሜት በጥልቅ መንካታቸዋ አልቀረም። ለዚህም ምክንያቱ ባይደን ወደ ሥልጣን ሲመጡ በአስተዳደራቸው አባላት መካከል የሚታይ ማንኛውንም ማንኛውም ዓይነት ንቀት የተንፀባረቀበት አቀራረብ ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ ለመውሰድ እና የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ያሳዩት ከነበረው አጉል የሚሰኝ አቀራረብ እና አፀያፊ የተባለ አነጋገር የተለየ ሁኔታ ለመፍጠር ቃል በመግባታቸው ነው።

XS
SM
MD
LG