በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ እና የዛምቢያ ግንኙነት


ተመራጩ የዛምቢያ ፕሬዚዳንት ሃካይንዴ ሂቺሌማ
ተመራጩ የዛምቢያ ፕሬዚዳንት ሃካይንዴ ሂቺሌማ

የዩናይትድ ስቴትስ የዓለም አቀፍ ልማት ተራድዖ ድርጅት/ዩኤስአይዲ/ አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር ለተመራጩ የዛምቢያ ፕሬዚዳንት የእንኳን ደስ ያለዎ መልዕክት አስተላለፉ።

መስሪያ ቤታቸው ባወጣው መግለጫ መሰረት ሳማንታ ፓወር እና አዲስ ተመራጩ ፕሬዚዳንት ሃካይንዴ ሂቺሌማ ባደረጉት ውይይት መንግሥቱ ሂቼሊማ በበርካታ አካባቢዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ እንዳያካሂዱ ያደረገ ቢሆንም የሀገሪቱ ሲቪል ማኅበረሰብ ተቋማት የምርጫውን ሂደት በንቃት መከታተላቸው ውጤቱ በስፋት ተቀባይነት እንዲያገኝ ማደረጉን አንስተዋል።

አዲስ ተመራጩ ፕሬዚዳንት ሙስናን ለመዋጋት፣ ዲሞክራሲያዊ እሴቶችን ለማጠናከር፣ የፕሬስ ነጻነት እና የሲቪል መብቶች ለማስከበር ስላላቸው ዕቅድ መወያየታቸውን ቃል አቀባዩ አውስተዋል።

ኮቪድ-19ን በጋራ ለመዋጋት እንዲሁም የዛምቢያ ኢኮኖሚ እንዲያንሰራራ አብረው ለመስራት ቃል መግባታቸውን መግለጫው አክሏል።

XS
SM
MD
LG