በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የባይደን አስተዳደር በዩናይትድ ስቴትስ ምድር የሶላር ኃይልን ማስፋፋት ጀምሯል


ፎቶ ፋይል፦ ጆ ባይደል የሶላር አገልግሎት ፕሮጀክቶች ልማትን ጉብኝት በፕሊማውዝ፣ ኒው ሃምፕሻየር፣ ሰኔ 4፣ 2019
ፎቶ ፋይል፦ ጆ ባይደል የሶላር አገልግሎት ፕሮጀክቶች ልማትን ጉብኝት በፕሊማውዝ፣ ኒው ሃምፕሻየር፣ ሰኔ 4፣ 2019

የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት የፕሬዚዳንት ባይደንን የአየር ንብረት ለውጥ አጀንዳዎች ውስጥ አንዱ የሆነውን የተፈጥሮ ኃይል አጠቃቀም ተግባራዊ ለማድረግ በካሊፎርኒያና ምዕራብ ዩናይትድ ስቴትስ ክፍለ ግዛቶች ውስጥ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ማጽደቃቸውን አስታወቁ፡፡

በካሊፍሮኒያው ውስጥ በጸሀይ ብርሃን ወይም ሶላር የሚሰሩ ሁለት ፕሮጀክቶችን እንዲሁም በምዕራባዊ የዩናይትድ ስቴት ግዛቶች ለተጨማሪ ሶስት የሶላር አገልግሎት ፕሮጀክቶች ልማት የሚውሉ የህዝብ የመሬት ይዞታዎችን በማዘጋጀት ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

እነዚህ ፕሮጀክቶች፣ ከቅሪተ አካል የሚገኙ የኃይልና ነዳጅ ምንጮችን እንደ ነፋስና የጸሀይ ብርሃን ወደ መሳሰሉ ተፈጥሯዊ የኃይል ምንጮች ለመለወጥ የታሰበው፣ የፕሬዚዳንት ባይደን ትልቁ አጀንዳ አካል መሆናቸው ተመልክቷል፡፡

በምስራቅ ካሊፍሮኒያ ሎስ አንጀለስ ውስጥ በሚገኘው የሪቨር ሳይድ ወረዳ ውስጥ፣ ከጸሀይ ብርሃን የተሰሩት የሶላር ሃይል ማመንጫዎች፣ 132ሺ ለሚሆኑ ቤቶች በቂ ኃይል የሚሰጡ መሆኑናቸውም ተገልጿል፡፡

በሌላም በክኩል በኮሎራዶ ኔቫዳና ኒው ሜክስኮ ግዛቶች ለተፈጥሮ ታዳሽ ኃይል ምንጮች የሚሆኑ ቦታዎችን ለማዘጋጀት እየተሰራ መሆኑ ተነግሯል፡፡

የባይደን አጀንዳ ለተፈጥሮ ታዳሽ የጸሀይና የነፋስ ኃይል ቅድሚያ መስጠት ይገባል የሚል ሲሆን ከከሰልና ከነዳጅ በማግኘት ላይ ትኩረት ማድረግን ከሚያስቀድመው ከቀደሞ የፕሬዚዳንት ትራምፕ አስተዳደር የተለየ መሆኑም ተዘግቧል፡፡

XS
SM
MD
LG