በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን በምክር ቤቱ ንግግራቸው ለመንግሥትና ዲሞክራሲ ተሟግተዋል


ፕሬዚዳንት ባይደን  ለምክር ቤቱ ንግግራቸውን ሲያሰሙ ፣ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለት ሴቶች ፕሬዚዳንቱን አጅበው ከአጠገባቸው ቆመዋል፡፡ ሁለቱ ሴቶች ምክትል ፕሬዚዳንት ከማላ ኸሪስና የተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ፣ ናንሲ ፐሎሲ ናቸው፡፡
ፕሬዚዳንት ባይደን  ለምክር ቤቱ ንግግራቸውን ሲያሰሙ ፣ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለት ሴቶች ፕሬዚዳንቱን አጅበው ከአጠገባቸው ቆመዋል፡፡ ሁለቱ ሴቶች ምክትል ፕሬዚዳንት ከማላ ኸሪስና የተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ፣ ናንሲ ፐሎሲ ናቸው፡፡

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ በትናንትናው ረቡዕ ምሽት፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በጋራ ምክር ቤቶቹ ፊት ተገኝተው፣ ባሰሙት ንግግራቸው፣ ስለ መሠረተ ልማት እና የሥራ እድል ማስፋፊያ ትልማቸው ተናግረዋል፡፡ መንግሥትንም መልካም ነገሮችን ሊሠራ እንደሚችል ጥሩ ተቋም አድርገው አቅርበዋል፡፡ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ የተነሳ የአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች አቀራረብ የተለየ መልክ እየያዘ መምጣቱም ተስተውሏል፡፡

ዝግጅቱ የተለመደው የወግ ሥነ ሥርዓቱ አልተለየውም፡፡ በኮቪድ 19 ወረርሽ የተነሳ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለጋራ ምክር ቤቶቹ አባላት ባሰሙት የመጀመሪያው ንግግራቸው ላይ የተገኙት እንግዶች፣ እንደወትሮው ወደ 1ሺ 600 ሰዎች ባይሆኑም 200 ያህል ሰዎች ታድመዋል፡፡

የፕሬዚዳንቱ ዋነኛ ንግግር ያተኮረው በአሜሪካውያን ላይ ሲሆን፣ አሁንም ቢሆን ዴሞክሪሲም ሊሰፍን፣ መንግሥትም የሚጠበቅበትን ሊሠራ እንደሚችል በመግለጽ የሚከተለውን ተናግረዋል፦

“መላ አገሪቱን እያስከተብን ነው፡፡ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የሥራ እድሎችን እየፈጠረን ነው፡፡ ሰዎች በራሳቸው ህይወት አይተው የሚያረጋግጡትን ውጤት እያስመዘገብን ነው፡፡ የእድል በሮችን እየከፈትን ነው፡፡ ለፍትህና ፍትሃዊነት ዋስትና እየሰጠን ነው፡፡”

ባይደን ለአሜሪካ የቤተሰብ እቅድ፣ ለትምህርት እና ለህጻናት እንክብካቤ ማስፋፊያ የሚውል ያወጡትን የ1.8 ትሪሊዮን ዶላር እቅዳቸውን አስተዋውቀዋል፡፡ ገንዘቡንም በከፊል የበለጸጉ አሜሪካውያን ላይ ከሚጥሉት ቀረጥ ለማግኘት ያሰቡ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ባይደን በምክር ቤቱ ንግግራቸው ለመንግሥትና ዲሞክራሲ ተሟግተዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:57 0:00

ይህ እቅዳቸው ባለፈው መጋቢት ለመሠረተ ልማት ማስፋፊያ ካቀረቡት የ2.3 ትሪሊዮን ዶላር ጥቅል በጀት ሌላ መሆኑን ነው፡፡ ስለ እቅዳቸው ሥራ ፈጠሪነት ሲናገሩም

“የአሜሪካውያን የሥራ እቅድ ጥረው ግረው የሚያድሩትን ሠራተኞች በማቀፍ አሜሪካን ለመገንባት የወጣ እቅድ ነው፡፡”ብለዋል፡፡

ባይደን በምክር ቤቱ አባላት ፊት ያደረጉት የመጀመሪያቸውን ንግግራቸው ከሌሎቹ ፕሬዚዳንቶች አንጻር ሲታይ ዘግይቶ የተደረገ ነው፡፡

ይሁን እንጂ መዘግየቱ የተፈጠረው በአገሪቱ እየተካሄድ ያለውን የክትባት መርሃ ግብር ቅድሚያ በመስጠት ሳይሆን የደህንነት ስጋት በመኖሩ ነው፡፡ ከአራት ወራት በፊት የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች፣ የምክር ቤቶቹን ህንጻ በመውረር፣ የባይደንን የምርጫ ድል ለመቀልበስ ጥረት ማድረጋቸው የሚታወስ ነው፡፡

ባይደን ይህንንም ጠቅሰውታል

“ከእርስ በርሱ ጦርነት በኋላ በዲሞክርሲያችን ላይ የተፈጸመ ትልቁ ጥቃት ነው፡፡”

ፕሬዚዳንት ባይደን አጀንዳዎቻቸውን አስመልከቶ አሁን ያደረጉት ንግግር፣ የትራምፕ ደጋፊዎችን ጨምሮ ለሁሉም አሜሪካውያን የተደረገ ነው፡፡

በጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ አስተዳደር ፕሮግራም ዳይሬክተር ታድ ቤልት የሚከተለውን አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

“ ፖሊሲያቸውን ያቀናጁት እንደ አርበኛ ተፎካካሪ ሆነው ነው፣ ያን ተቃውሞ ማን ሊቆም ይችላል? የመሠረተ ልማት እቅዳቸውን ያወጡት የአሜሪካ ሥራ ፈጣሪ እቅድ አድርገው ነው፣ ስለ ሥራ እድል ፈጠራም ደጋግመው አውርተዋል፡፡ እና ታዲያ እነዚህን እቅዶችን ተቃውሞ እሚቆም ማን ሊሆን ይችላል?”

ባይደን የመሳሪያ ህጉን ጨምሮ በሜክስኮ ድንበር በኩል እየጨመረ የመጣው የስደተኞች ቁጥር በሚታይበት በዚህ ወቅት፣ የስደተኞን ረቂቅ ህግ፣ የምክር ቤት አባላቱ እንዲያጽደቁ በድጋሚ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

ባይደን በውጭ ግንኙነትም ፖሊሲው ንግግራቸውም፣ የአሜሪካ ጦር ከአፍጋኒስታን ስለመውጣቱ፣ የሰሜን ኮሪያ እና ኢራን በኩል ስላለው የኒዮክለር ስጋት፣ እንዲሁም የራሽያን ጠብ አጫሪነትን ለመመከት ስለሚደረገው ጥረት አስረድተዋል፡፡

የቻይና ፕሬዚዳንት ዥ ጂፕንግ፣ ቻይንና በዓለም እጅግ አደገኛ ወደ ሆነው ሁኔታ ውስጥ እየመሯት መሆኑን በመግለጽ ያስጠነቀቁ ሲሆን፣ የዩናትይድ ስቴትስ ባላንጣዎችም የአሜሪካን ህዝብ ለመከፈፋፈል የሚያደርጉት ያልተሳካ ጥረት መኖሩንም በመጥቀስ የሚከተለውን ብለዋል፦

“በአሜሪካ ምክርቤት ህንጻ ላይ የተፈጸመውን የአመጽ ጥቃት የተመለከቱት በአሜሪካ ዴሞክራሲ ላይ ዥንበር እንዳዘቀዘቀች ነው፡፡ ይሁን እንጂ ግን ተሳስተዋል፡፡”

እስከዛሬ በነበረው ልማድ መሰረት፣ ቀዳማይ ዕመቤት ጂል ባይደን፣ የፕሬዚዳንቱን አጀንዳ የሚያጎሉ እንግዳ አፈላልገው አላመጡም፡፡ ይልቁንም ስደተኛ የሆኑትን ነርስ፣ ለመሳሪያ ህጉ ጥብቅና የቆሙትን ሰውና፣ የጾታ ለውጥ ያካሄዱትን አንድ ታዳጊ ወጣት በድረገጽ እንዲቀርቡ አድርገዋል፡፡

ብቸኛው ጥቁር የሪፐብሊካን ሴንተር የሆኑት ቲም ስካት፣ በባይደን አንጻር የሪፐብሊካንን ምላሽ በንግግር አሰምተዋል፡፡

ባይደን ስለክትባቱ ያሰሙትን ንግግርም በማዋደቅ የሚከተለውን ብለዋል፡፡

“የተፋጠነ የክትባት ሂደት እንዲፈጠር ላስቻለውና “Operation Warp Speed” ለተባለው የትራምፕ አስተዳደር ሥራ ምስጋና ይግባውና አገሪቱ ውጤታማና አስተማማኝ በሆኑ ክትባቶች ተጠለቅልቃለች፡፡

ፕሬዚዳንቱ ለምክር ቤቱ ንግግራቸውን ሲያሰሙ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለት ሴቶች ፕሬዚዳንቱን አጅበው ከአጠገባቸው ቆመዋል፡፡

በአገሪቱ ፕሬዚዳንት ላይ አንድ እክል ቢደርስ፣ በተተኪው የሥልጣን ተዋረድ በአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ በቅድመ ተከተል ተሰልፈው የሚገኙት፣ ምክትል ፕሬዚዳንት ከማላ ኸሪስና የተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ፣ ናንሲ ፐሎሲ ናቸው፡፡

ይህ በዩናይትድ ስቴትስ የፖለቲካ ታሪክ አብይ ሥፍራ ይኖረዋል፡፡

(በቪኦኤ የዋይት ሐውስ ዘጋቢ ፓትሲ ውዳክስዋራ ካጠናቀረችው ዘገባ የተወሰደ፡፡)

XS
SM
MD
LG