በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን በ100 ቀናት ለአፍሪካ ያደረጓቸው ጥቂት ትላልቅ ነገሮች


በወቅቱ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት የዛሬው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እኤአ 2014 ዋሽንግተን ዲሲ ላይ ለሶስት ቀናት በተካሄደውና ወደ 50 የሚጠጉ የአፍሪካ መሪዎች በተገኙበት ዩናይትድ ስቴትስ እና አፍሪካ የንግድ ጉባኤ ላይ ተገኘተው ንግግር ሲያሰሙ
በወቅቱ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት የዛሬው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እኤአ 2014 ዋሽንግተን ዲሲ ላይ ለሶስት ቀናት በተካሄደውና ወደ 50 የሚጠጉ የአፍሪካ መሪዎች በተገኙበት ዩናይትድ ስቴትስ እና አፍሪካ የንግድ ጉባኤ ላይ ተገኘተው ንግግር ሲያሰሙ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ የመጀመሪያውን 100 ቀናቸውን የፈጁት ሙሉ ኃይላቸው በአሜሪካው ውስጥ በተከሰተው የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ላይ በማዋል ነው፡፡ እልህ አስጨራሽ በነበረው በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ግን በአፍሪካ ውስጥ ተቀባይነትን ያገኙ ጥቂት ነገሮችን አድርገዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ወደ ሥልጣን በመጡበት የመጀመሪያው ቀናቸው ዩናይትድ ስቴትስ ከዓለም የጤና ድርጅት ለመውጣት የነበራትን እቅድ እንድታቆም አድርገዋል፡፡

ባይደን ከሳቸው በፊት የነበረው አስተዳደር ከዓለም አቀፉ የጤና ተቋም ለመውጣት የወሰነውን አወዛጋቢ ውሳኔ መቀልበሳቸው ዓለም አቀፋዊ ድጋፍ አስገኝቶላቸዋል፡፡

በተለይ የአፍሪካ የጤና ኃላፊዎች ውሳኔውን በጤናው ረገድ በዓለም ፍትሃዊ ስርዓት እንዲኖር ያደርጋል ብለውታል፡፡

ባይደንም ለድሆቹ አገሮች የክትባት ስርጭቱ እንዲዳደረስ፣ ለኮቫክስ ክትባት ስርጭት የ2ቢሊዮን ዶላር ተጨማሪ እርዳታ ጠይቀዋል፡፡

ሥልጣን በያዙ 90ኛ ቀናቸው ላይ፣ እኤአ ሚያዝያ 20 ያስተላለፉት መልዕክትም፣ ከውቂያኖሱ ባሻገር ባለው የዓለም ክፍል አስተጋብቷል፡፡

በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዳለ ህይወቱ ባለፈው ፣ የሚኒያፖልሱ ነዋሪ፣ ጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ተከሶ የነበረው የፖሊስ መኮንን ላይ፣ የጥፋተኝነት ውሳኔ በተላለፍበት ወቅት ፕሬዚዳንት ባይደን ሲናገሩ እንዲህ ብለው ነበር

“ይህን አጋጣሚ ሥራችንን አከናውነን ጨርሰናል ብለን እንዲሁ ልንተወው አይገባም፡፡ በደንብ ልንመለከተው ይገባናል፡፡ ልብም እንድንለው ያስፈልገናል፡፡ እነዚያን 7 ደቂቃ ከ29 ሰኮንዶች እንደተመለከትናቸው አድርገን ልናየው ይገባናል፡፡ መስማትም ይኖርብናል፡፡ “መተፈንስ አልቻልኩም መተንፈስ አልቻልኩም!” እነዚያ የጆርጅ ፍሎይድ የመጨረሻ ቃላት ነበሩ፡፡ እነዚያ ቃላት ከሱ ጋር አብረውት እንዲሞቱ ማድረግ አንችልም፡፡ እነዚያን ቃላት መስማታችንን መቀጠል አለብን፡፡

ባይደን በ100 ቀናት ውስጥ ለአፍሪካ ያደረጓቸው ጥቂት ትላልቅ ነገሮች
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:17 0:00

ፍሎይድ በሂውስተን ተወልዶ፣ በሚኒያፖልስ የተገደለ ጥቁር አፍሪካ አሜሪካዊ ነው፡፡ ፍሎይድን ለህልፍት አብቅቷል በተባለው የቀድሞ የፖሊስ መኮንን ደሪክ ሻቭን ላይ ፣ የጥፋተኝነት ውሳኔ ሲተላለፍበት፣ መላው አፍሪካ ሂደቱን የተከታተለው በጭንቀት ውስጥ ሆኖ ነበር፡፡

ባለፈው ዓመት በሻቭን ጉልበት ሥር ሆኖ እስትፋንሱ እስክታልፍ በተራዘመ ጭንቅ የታፈነው ፍሎይድ፣ የሚወዳቸው ሁሉ እንዲያስጥሉት እየተማጸነ ሲጮህ ታይቷል፡፡

ያ ትዕይንት ተቃውሞን የቀሰቀሰ ሲሆን በዩናይትድ ስቴትስ የፖሊስ አሠራር ደንብ እንዲሻሻልም የጠየቀ ነበር፡፡

በደቡብ አፍሪካ የብዝህነት አስልጣኝ የጾታና ዘር ጉዳዮች ተራማሪ የሆኑት፣ እንደ አሳንዳ ጓሸኜ የመሳስሉት አፍሪካዊ ተንታኞች፣ የዘር መድልዎ ችግር መኖሩን አምኖ በመቀበል፣ ባይደን ለአሜሪካ ህዝብ ያሰሙትን ንግግር ደግፈውታል፡፡

ደቡብ አፍሪካም ብትሆን፣ ለመቶ ዓመታት ተንሰራፍቶ ከቆየው የቅኝ ገዥነት፣ ጨካኝና ዘረኛው የአፓርታይድ መንግሥት በኋላ፣ አሁን ድረስ ካለባት የዘር መድልዎ ችግሮች ለመላቀቅ እየታገለች ያለች አገር ናት፡፡

አሳንዳ ጨምረው እንደተናገሩት፣ ምክትል ፕሬዚዳንቷ ከማላ ኸሪስ ተሰሚነት እንዳላቸው ጥቁር ሴት በመሆናቸው፣ ባይደን የዘር መድልዎን ለመታገል ለሚያደርጉት ጥረት ክብደት እንዲኖረው ያደርጉታል ይላሉ፡፡ ይሁን እንጂ ከአስተዳደሩም ሆነ ከአሜሪካ ተቋማት ብዙ ነገር እንደሚጠብቁ ተናግረዋል፡፡

“ከማላ ኸሪስን እናደንቃለን፡፡ እሳቸውን ማደናቃችንም ጥሩ ነገር ይመስለኛል፡፡ ይሁን እንጂ ግን መዋቅራዊ ዘረኝነት በተዘረጋበት መዋቅር ውስጥ ያለው ባለቀለም ሰው ለውጥ ማምጣት የሚችልበት እድል እጅግ እጅግ አነስተኛ ነው፡፡

ስለዚህ ሥርዓቱን እና አድሏዊነትን ባለበት እንዲቆይ የሚያደርገውን መዋቅር እስካልታገልነው ድረስ በዩናይትድ ስቴትስም ሆነ በመላው ዓለም ለውጥ የምናይ አይመስለኝም፡፡ ስለዚህ አዎ እውነትነ ነው ለአሜሪካና ለባይደን ጥሩ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ግን ሊያመጡት ስለሚችሉት መዋቅራዊ ለውጥ መናገር ትችላላችሁ? “

መሰረቱን በጆሀንስበርግ ያደረገው የተንታኙ ብሩክስ ስፔክተር ባይደን ተችዎች፣ ፕሬዚዳንት ትራምፕ የአፍሪካን ፖሊሲ አስመልከቶ ያደረጉት ስር ነቀል ወይም ትልቅ ለውጥ የለም ብለው ይተቹ እንደነበሩት ሁሉ፣ ባይደንም መተቸታቸው በራሱ አንድ ተፈላጊ ለውጥ ነው ይላሉ፡፡

“በዩናይትድ ስቴትስ የንግድ ልውውጥ ማእቀፍ ውስጥ ያለውን የአፍሪካን የእድገት አማራጭ ድንጋጌ (አጎዋ) ማጠናከር አስፈላጊ ነው፡፡”

“በየጊዜው ድንገት እየተቆራረጡና እየተለዋወጡ ከሚደረጉ የፖሊሲ ለውጦች ይልቅ መሬት ይዘው በዝግታ በረጋና ዘላቂ በሆነ መንገድ ነገሮችን ማከናወን ተመራጭ ነው፡፡ በአህጉሪቱ የኢኮኖሚ ለውጥ እንዲመጣ ድጋፍን መስጠት ከፈለግ ከፈልክ በአህጒሪቱ የኢኮኖሚ እድገት የሚያጠናክር ፖሊስን ማውጣት ነው፡፡”

ለበርካታ ዓመታት የአሜሪካን ዲፕሎማት ሆነው በውጭው ዓለም ያገለገሉት ስፔክተር “ባይደን በአፍሪካ ላይ የሚያሳድሩት ተጽእኖ በጊዜ ሂደት የሚታይ ይሆናል፡፡”

“የፕሬዚዳንቶች ታሪክና አበርክቶ የሚገነባው በዓመታት ሥራቸው እንጂ በቀናት አይደለም፡፡ 100 ቀናት እንኳ ቢሆኑትም ማለት ነው፡፡” ብለዋል፡፡

(የቪኦኤ ዘጋቢ አኒታ ፖል ከጆሀንስበርግ ከላከችልን ዘገባ የተወሰደ)

XS
SM
MD
LG