በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን በሩሲያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀቦችን ጣሉ፤ ወታደሮች ላኩ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን

ሩሲያ ዩክሬንን በመውረሯ ምክንያት ዩናይትድ ስቴትስ በሩሲያ ባንኮችና ከበርቴዎች ላይ ተጨማሪ ማዕቀቦች መጣሏንና ተጨማሪ ወታደሮችን ወደ አውሮፓ እየላከች መሆኗን አስታወቀች።

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ዛሬ ከሰዓት በኋላ ዋይት ሃውስ ውስጥ ባደረጉት ንግግር ሃገራቸውና አጋሮቿ “የሩሲያን በዓለም አቀፍ ምጣኔ ሃብት ውስጥ የመሳተፍ አቅም ለመገደብና መስኮብ ለጦሯና ጦሯን ለማሳደግ የምታውለውን ገንዘብ ለማሳጠር ያስችላሉ” ያሏቸውን እርምጃዎች ዘርዝረዋል።

እነዚህ እርምጃዎች በአሜሪካዊያን ላይ ለተወሰነ ጊዜ የኢነርጂ ዋጋ ንረት ሊያስከትሉ እንደሚችሉ ፕሬዚዳንቱ ጠቁመው ይህ “የሃገራቸውን መርኆች ጠብቆ ለማቆየት የሚከፈል ዋጋ” መሆኑን አመልክተዋል።

“አሜሪካ ሁከተኞችን ትጋፈጣለች፤ ለነፃነት እንቆማለን፤ እኛ ማለት ይህ ነን” ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።

በፕሬዚዳንቱ ትዕዛዝ ሰባት ሺህ የሚሆኑ ተጨማሪ የዩናይትድ ስቴትስ ጦር አባላት ወደ አውሮፓ እየሄዱ መሆናቸውን የመከላከያ መሥሪያ ቤቱ አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG