በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ገና ተበሠረ


ዌስት ባንክ ውስጥ በምትገኘው ቤተልሄም ወንድና ሴት ስካውቶች ማንጀር አደባባይ ላይ ባደረጉት የበዐል ሠልፍ ገናን አብሥረዋል፡፡

የፍልስጥዔምን ባንዲራ እያውለበለቡ የተሰለፉት ስካውቶች ከጥንታዊቱ የቅዱስ ፅንሰት ቤተ ክርስትያን ፊት ለፊት በተተከለችና በወርቃማ ጌጣጌጥ ባሸበረቀች የገና ዛፍ ፊት አልፈዋል፡፡

በሺሆች የሚቆጠሩ ከዓለም ዙሪያ የተጓዙ ምዕመናን ይህንን የአደባባይ ትዕይንት እየተከታተሉ ሲሆኑ ሌሎች ደግሞ ኢየሱስ የተወለደበትን ዋሻ ለማየት በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በተገነባችው ቤተ ክርስትያን ውስጥ በሰልፍ ተኮልኩለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG