ዋሺንግተን ዲሲ —
የቀድሞዋ የቅንጅት አመራር አባልና የአንድነት መሪ ወይዘሪት ብርቱካን ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ሲደርሱ ሞቅ ያለ አቀባበል ነው የጠበቃቸው።
በራሳቸው አነሳሽነት ሥነ ሥርዓቱን ማዘጋጀታቸውን የገለጹት ወጣቶች “ብርቱካን ገና ከማለዳው ለሌሎች ሕይወት መስመር መያዝ ራሷን ማስቀደም የቻለች መሪ ናት” ይላሉ።
የቀድሞ የቅንጅት አመራር አባል የኪነ ጥበብ ባለ ሞያው አርቲስት ደበበ እሸቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ተገኝተው ወ/ሪት ብርቱካንን ከተቀበሉ ታዋቂ ግለሰቦች አንዱ ነው።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ