በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በረከት ስምዖን፤ መለስ በጣም ተሽሏቸዋል አሉ


በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጤንነት ላይ አሉባልታ ሲሉ ለገለፁት ለያንዳንዱ ዘገባ መልስ አልሰጥም ሲሉ የኢትዮጵያ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ በረከት ስምዖን ተናገሩ፡፡

(ይህ ገፅ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ኮምፕዩተርዎ ከአንድ በላይ ድምፅ ማጫወቻ አለው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ ፅሁፍ ሥር ካሉት ማጫወቻዎች አንደኛውን ብቻ አስቀርተው ሌሎቹን ያቁሟቸው፡፡)

ሚኒስትሩ በዚሁ መግለጫቸው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጤንነት እየተሻሻለ መምጣቱን ቢገልፁም ሪፖርተር ጋዜጣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የት እና በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ላቀረበው ጥያቄ መልስ ሳይሰጡ አልፈዋል፡፡

አቶ በረከት ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የጤንነት ሁኔታ በጣም በጥሩ የጤንነት ሁኔታ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

(ገፁ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ከዚህ ሥር ካሉት ማጫወቻዎች አንደኛውን ብቻ አስቀርተው ሌሎቹን ያቁሟቸውና የሚጫወተውን እንደገና ያስጀምሩት፡፡ )


XS
SM
MD
LG