በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያው ምርጫ ዲሞክራስያዊና የህዝብ ተቀባይነት ያለው ነው ሲሉ በረከት ስምኦን አስታወቁ


“የዩናይትድ ስቴይትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም፥ ዋይት ሀውስም ሆነ ማንም ከኢትዮጵያ ህዝብ ውሳኔ ጋር አብሮ መኖር መጀመር አለበት” ብለዋል

የመንግስት ኮሙኒኬሽንስ ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሚኒስትር አቶ በረከት ስምኦን ባለፈው እሁድ ለአራተኛ ጊዜ የተካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ የህዝብ ተቀባይነት ያለው በመሆኑ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም፥ ዋይት ሀውስም ሆነ ማንም ከሁኔታው ጋር አብሮ ለመኖር መላመዱ ይጠቅማል ብለዋል።

ሚኒስትር በረከት የኢትዮጵያ መንግስት ምርጫው እንዲያከናውነው የቀየሰው እቅድ ተፈጽሟል። መንግስት ምርጫው ዴሞክራስያዊ፥ ሰላማዊና የህዝብ ተቀባይነት ያለው እንዲሆን ነበር ያቀደው። እነዚህ ሶስት ቁምነገሮችም በምርጫው ሂደት ተሟልተዋል ብለዋል።

በረከት ስምኦን
በረከት ስምኦን

የመንግስቱ ቃል አቀባይ ይህን ያሉት ግንቦት 15 ቀን 2002 አም ስለተካሄደው አገር አቀፍ ምርጫና ስለውጤቱ ዛሬ ማለዳ በጽህፈት ቤታቸው ለጋዜጣኞች በሰጡት መግለጫ ነው።

አቶ በረከት በምርጫ ታዛቢዎችና በሌሎችም ስለሚሰሙ ትችቶች ሲናገሩ “በኢትዮጵያ ከተሰማሩ የምርጫ ታዛቢዎችና በሩቅ ከሚገኙ አካላት የተለየዩ ዘገባዎች እየወጡ ናቸው።ያም ሆነ ይህ ግን ኢትዮጽያ ነጻ፥ ፍትሀዊ ዲሞክራስያዊና የህዝብ ተቀባይነት ያለው ምርጫ እንዳካሄደች በጽኑ ታምናለች። “ይህም የመንግስት አመለካከት ነው” ብለዋል።

አያይዘውም ሚኒስትሩ የዩናይትድ ስቴይትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም፥ ዋይት ሀውስም ሆነ ማንም ከኢትዮጵያ ህዝብ ውሳኔ ጋር አብሮ መኖር መጀመር አለበት። ለማንም ቢሆን የህዝብን ምርጫ መጠራጠር አይጥቅምም ሲሉ አስገንዝበዋል።

XS
SM
MD
LG