በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቤንሻንጉል ክልል ግጭት ዛሬም ስድስት ሰዎች መጎዳታቸው ታውቋል


አሶሳ ከተማ የነበረው ግጭት
አሶሳ ከተማ የነበረው ግጭት

የአሶሳ ከተማ ከንቲባ በዛሬው ዕለት የቆሰሉ ሰዎች አሶሳ ከተማ ሆስፒታል መግባታቸውን ተናግረዋል።

በክልሉ ለተቀሰቀሰው ግጭት በገንዘብ የተደለሉ ሰዎች እጅ እንዳለበትና በድርጊቱ የተጠረጠሩ 40 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ አሻድሌ ሃሰን አስታውቀዋል።

የአሶሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ቶፊቅ አብዱልቀይም በበኩላቸው በዛሬው ዕለት ከከተማዋ ወጣ ብሎ ከሚገኝ የገጠር ቀበሌ የቆሰሉ ሰዎች እንደመጡ ተናግረዋል።

በዚህ ግጭት ክልሉ ዐስር ሰዎች እንደተገደሉ ሲያስታውቅ የአሜሪካ ድምፅ ከተለያዩ ቦታዎች ያገነው መረጃ ዐስራ ሁለት ሰዎች መገደላቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

ጽዮን ግርማ ከአሶሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ቶፊቅ አብዱልቀይም ጋራ ያደረገችውን አጭር ቆይታ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በቤንሻንጉል ክልል ግጭት ዛሬም ስድስት ሰዎች መጎዳታቸው ታውቋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:35 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG