በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሶሳው ግጭት


አሶሳ ከተማ የነበረው ግጭት
አሶሳ ከተማ የነበረው ግጭት

በግጭቱ የሰው ሕይወት መጥፋቱና መቁሰሉን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የዛሬው ግጭት ትናንትናና ከትናንት በስቲያ በአሶሳ ከተማ የተከሰተውን ተከትሎ መቀስቀሱን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። ነባር ብሔረሰብ ከሚባሉት ውስጥ የተደራጁ ወጣቶች በስብጥር የሚኖሩ የተለያየ ብሔረሰብ አባላት ላይ ለሁለት ቀናት ድብደባ፣ንብረት ማውደውምና ግድያ መፈፀማቸውን የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ይገልፃሉ።
የክልሉ መንግሥትም ሆነ የፀጥታ አካላት “እቤት ውስጥ ቁጭ በሉ” ከሚል ማሳሰቢያ ውጪ ምንም መፍትሔ ባለመስጠታቸው በዛሬው ዕለት ደግሞ የከተማው ነዋሪዎች በብዛት በአንድ ላይ ሆነው “መንግሥት ካልተከላከለልን ራሳችንን እንከላከላለን” በሚል በአንድ ላይ አደባባይ መውጣታቸው ያነጋገርናቸው የተለያዩ ነዋሪዎች አረጋግጠዋል።
በዚህም ከፍተኛ የሆነ ግጭት መፈጠሩንና የፌደራል ፖሊስ ገብቶ ነገሩን እስኪያበርደው ድረስ ከየት እንደሆነ የማይታወቅ ተኩስ በሰልፈኞቹ ላይ ሲተኮስ እንደነበረም ተናግረዋል።
የቤንሻንጉል ክልል ባለሥልጣናትን ለማነጋገር እየሞከርን ነው።

(ጽዮን ግርማ ያጠናቀረችው ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

የአሶሳው ግጭት
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:16 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG