በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ የደረሰ ጥቃት


በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ትናንት ከሰዓት በኋላ በተፈፀመ ጥቃት ከአምስት ሰዎች በላይ መገደላቸውን የክልሉ ፀጥታና ሰላም ግንባታ ቢሮ አስታውቋል።

ጥቃቱን ተከትሎ 11 ሰዎች ቆስለው በፓዌ ሆስፒታል የህክምና ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን የቢሮው ኃላፊ አቶ አበራ ባየታ ለቪኦኤ ገልፀዋል።

“ጥቃቱ የተፈፀመው የገነተ-ማርያም ቀበሌ ምክትል ሊቀመንበር ባለፈው ቅዳሜ ባልታወቁ ሰዎች በጩቤ በመወጋታቸው ነው” ያሉት የቢሮው ኃላፊ የርሳቸው ዘመዶች አፀፋውን ለመመለስ የፈፀሙት ጥቃት መሆኑን እንደሰሙ ተናግረዋል።

ጥቃቱ “የቆዳ ቀለምን ለይቶ የተፈፀመ ነው” የተባለውም ሃሰት እንደሆነ ገልፀዋል።

አሁን “በቀበሌውም በወረዳውም የመንግሥት የፀጥታ ሃይሎች በመግባታቸው መረጋጋት ተመልሷል” ያሉት ሃላፊው ጥቃት ፈፃሚዎቹ ግን አለመያዛቸውን።

ባለፈው ሁለት ሳምንት በዳንጉር ወረዳ 57 ሰዎች መገደላቸውን ያስታወሱት አቶ አበራ በአማራ ክልል ጃዊ ወረዳም ከሁለት ወር በፊት ታጣቂዎች ብዙ ሰው መግደላቸውን አመልክተዋል።

ጥቃቱ በድንገት የተፈፀመ መሆኑን አቶ አበራ ጠቅሰው ችግሩ እንዳይባባስ ከአማራ ክልላዊ መንግሥት አመራር ጋር እየተወያዩና አብረውም እየሠሩ መሆናቸዋን ገልፀዋል። የተቋቋመው የማዘዣ ማዕከልም ሥራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

ቀድም ሲል በተፈፀሙ ጥቄቶች የተጠረጠሩ ከ16 በላይ ሰዎች መያዛቸውን ኃላፊው አመልክተው በማኅበራዊ መገናኛ የሚተላለፉ መረጃዎች በጣም የተጋነኑ በመሆናቸው ኅብረተሰቡ መረጃዎችን ከእውነተኛና ታማኝ ምንጮች እንዲፈልግም መልዕክት አስተላልፈዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG