በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በመንግሥትና ጉህዴን መካከል የተጀመረውን ሰላም ለማሳካት ተኩስ መቆሙ ተገለፀ


በመንግሥትና ጉህዴን መካከል የተጀመረውን ሰላም ለማሳካት ተኩስ መቆሙ ተገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:08 0:00

በመንግሥትና ጉህዴን መካከል የተጀመረውን ሰላም ለማሳካት ተኩስ መቆሙ ተገለፀ

በቤንሻንጉል ጉምዝ መተከል ዞን ውስጥ በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ላይ ከሚያዝያ 1 እስከ ሚያዝያ 7/ 2014 ዓ.ም ድረስ ተከፍቶብናል ያሉት ተኩስ ካለፈው ሳምንት ቅዳሜ ጀምሮ መቆሙን እና ላለፉት አራት ቀናትም ምንም ዓይነት የተኩስ ድምጽ አለመስማታቸውን የጉህዴን ሊቀ-መንበር አቶ ግራኝ ጉደታ ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።

የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መንግሥት በታጣቂዎቹ ላይ የተጀመረው የሕግ ማስከበር እርምጃው ለግዜው እንዲቆም የተደረገው በመንግሥትና ጉህዴን መካከል የተጀመረውን የእርቀ-ሰላም ሂደት የተሳካ ለማድረግ መሆኑን ገልጿል።

የክልሉ መንግሥት ኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ በየነ ቀድሞውንም "ተኩስ ተከፍቶባቸው ሳይሆን የሕግ ማስከበሩ እርምጃ ሲወሰድ የነበረው በታጣቂዎቹ የሚደረጉ ትንኮሳዎች በመኖራቸው ነው" ይላሉ።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG