በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተፈናቃዮች ወደ ቤኒሻንጉል ጉምዝ ተመለሱ


ከ50ሺ በላይ ተፈናቃዮች ወደ መተከል ዞን ተመልሰዋል ሲል የቤኒሻንጉል ጉምዝ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ። የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ታረቀኝ ታሲሳ እንዳሉት ተፈናቃዮቹ የተመለሱት የፀጥታ ሁኔታ በመሻሻሉ ነው።

በክልሉ ከ360ሺ በላይ ዜጎች በተለያዩ ምክንያቶች ተፈናቅለው በድጋፍ የሚኖሩ መሆኑንም አቶ ታረቀኝ ጨምረው ገልፀዋል።

የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ታረቀኝ ታሲሳ "ከመተከል ዞን በ2012 ዓ.ም. ሃምሌ ወር ውስጥ በፀጥታ ምክንያት ተፈናቅለው ከነበሩ መካከል አብዛኛዎቹ ተመልሰዋል" ሲሉ ገልፀዋል። እነዚህ ተፈናቃዮች ሰፍረው ከነበረበት አማራ ክልል ወደ መተከል እንዲመለሱ የተደረገበትን ምክንያትም ኮሚሽነሩ አስረድተዋል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ተፈናቃዮች ወደ ቤኒሻንጉል ጉምዝ ተመለሱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:40 0:00


XS
SM
MD
LG