አምቦ —
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዞን ግጭት በመቀስቀስ ተጠርጥረው የታሰሩ 98 ሰዎች የፍርድ ሂደት አንድ ዓመት ከ10 ወራት በላይ ተጓቷል ሲሉ የታሳሪ ቤተሰቦችና ዘመዶች አመለከቱ።
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ መከሰቱ የፍትህ አሰጣጥ ሂደቱ ላይ እንቅፋት ሆኖብናል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ጽህፈት ቤት የተቀናጀና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ምርመራ በክልሉ ግጭት በመቀስቀስ ፣ ህይወት በማጥፋትና ንብረት በማውደም ተጠርጥረው የተከሰሱ ግለሰቦች ቁጥር ከተጠቀሰውም በላይ መሆኑን ጠቅሰው የምርመራው ሂደት ከተከሳሾቹ ብዛት አንፃር ጊዜ ወሳጅ በመሆኑ ነው የዘገየው ሲሉ ተናግረዋል::
የኮሮና ቫይረስ ተጋላጭነትን በመቀነስ የክስ ሂደቱ ለመቀጠል መታሰቡንም አክለው ገልፀዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።