በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተፈናቀሉ በቂ ድጋፍ አለማግኘታቸውን ገለጹ


ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ካማሽ ዞን በሎ ጀገንፎይ ወረዳ ተፈናቃዮች በኦሮምያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ሳሲጋ ወረዳ ውስጥ ምቹ ባልሆነ ሁኔታ ሰፍረን እንገኛለን። በቂ ድጋፍ ባለማግኘታችንም ለችግር ተጋልጠናል አሉ። በበሎጀገንፎይ የተለያዩ ቀብሌዎች ውስጥ ታጥቀው ከክልሉ ፀጥታ ኃይሎች ጋር በሚዋጉ ሃይሎች ምክንያት መፈናቀላቸውንም አስታውቀዋል።

የክልሉ አደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን ከካማሽ የተለያዩ ወረዳዎች የተፈናቀሉት ሰዎች እጠቃላይ 95ሺ ሰዎች መሆናቸውን ጠቅሶ፤ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ከፌደራል አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ጋር በመስራት ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል። የምስራቅ ወለጋ ዞን አደጋ ስጋት አመራር ኮምሽን ፅህፈት ቤትም በበኩሉ "በሎጀገንፎይ ለተፈናቀሉ ሰብዓዊ ድጋፍ እየተደረገ ነው ብሏል።

በሌላ ዜና ካማሽ ዞን በሎጀገንፎይን ጨምሮ በሶስት ወረዳዎች ውስጥ የጉሙዝ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ጉህዴን/ ኃይሎች ጋር ውግያ እያካሄድን ነው 100 የሚሆኑ ታጣቂዎችንም ደምስሰናል" ያለው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፖሊስ ኮምሽን በበኩሉ "ኃይሎቹ ከህወሃት ጋር ግንኙነት ስላላቸው አገርን ለማፍረስ አልመው ነው የሚንቀሳቀሱት" ይላል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተፈናቀሉ በቂ ድጋፍ አለማግኘታቸውን ገለጹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:28 0:00


XS
SM
MD
LG