በቤኒሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን ዲባጢ ወረዳ ውስጥ በዚህ ሳምንት ውስጥ ከ100 በላይ የሚሆኑ ሰዎች መታሰራቸውን ከነዋሪዎችና ቤተሰቦቻቸው መካከል ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። ሰዎቹ የታሰሩት መንግሥት ሸኔ ብሎ የሚጠራቸውና እራሳቸውን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ብለው ከሚጠሩት ታጣቂ ቡድኖች ከመደገፍ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው መሆኑንም ገልጸዋል። የፌዴራል መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ "መንግሥት የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች እርምጃ ይወስዳል" ካሉ በኋላ በዲባጢም እየታሰሩ ያሉት መንግሥት ጸጥታና መረጋጋትን ለመመለስ የሚወስደው እርምጃ አካል መሆኑን ገልጸው ንጹሃንም ካሉበት እንደሚጣራ አስታውቀዋል።
የፕሮግራሙ ተከታታይ ክፍሎች
-
ጁን 10, 2023
የደም ግፊት መጠን ለምን ይጨምራል?
-
ጁን 09, 2023
የዓለም ምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ የርዳታ ምግብ ሥርጭቱን ማቆሙን አስታወቀ
-
ጁን 09, 2023
ከሱዳን ጦርነቱን የሸሹ ከ41ሺሕ በላይ ሰዎች ኢትዮጵያ ገቡ