በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"የኦነግ ሸኔን ታጣቂዎች ትደግፋላችሁ" በሚል የታሰሩ ፍ/ቤት አልቀረቡም


“የኦነግ ሸኔን ታጣቂዎች ትደግፋላችሁ” በሚል በቤኒሻንጉል ጉምዝ መተከል ዞን ውስጥ የተያዙ ሰዎች ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ከሦስት እስከ ስድስት ወራት መታሰራቸውን ቤተሰቦቻቸው ገልፀዋል።

ግለሰቦቹ በቡለንና ድባጤ ወረዳዎች ፖሊስ ጣቢያዎች እንዲሁም ግልገል በለስ ማረሚያ ቤት የሚገኙ ሲሆን ከመተከል ዞን አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ሥር ያሉት 1 ሺህ 137 ሰዎች መሆናቸውን የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ምክትል ኮሚሽነር ኮማንደር ምሥጋናው ኢንጂፈታ ለቪኦኤ ገልፀዋል።

659 ሰዎች ጉዳያቸው ውሳኔ ሳይሰጠው በግልገል በለስ ማረሚያ ቤት ለወራት ተይዘው እንደሚገኙና ይሄም የሆነው በዞኑ ውስጥ በሚታየው ያለመረጋጋት ሳቢያ ፖሊስ ማስረጃ አጠናቅሮ ለፍርድ ቤት ማቅረብ ባለመቻሉ መሆኑን ኮማንደር ምሥጋናው ተናግረዋል።

በመተከል ዞን የተለያዩ ወረዳዎችም 478 ሰዎች ፖሊስ ጣቢያዎች ውስጥ ታስረው እንደሚገኙና በመተከል ዞን የቀጠለው አለመረጋጋት የህግ ሂደቱን ለመቀጠል አዳጋች ሊያደርገው እንደሚችልም ምክትል ኮሚሽነሩ አመልክተዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

"የኦነግ ሸኔን ታጣቂዎች ትደግፋላችሁ" በሚል የታሰሩ ፍ/ቤት አልቀረቡም
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:44 0:00


XS
SM
MD
LG