በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የባለሞያዎች አስተያየት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ስለሚስተዋሉ ግጭቶች


በቤንሻንጉል ክልል መተከል ዞን ውስጥ ለሚስተዋሉ ሰብዓዊ ቀውሶች መነሻ የክልሉ ህገመንግሥት ለሌሎች ነዋሪዎች የባለቤትነት መብት መንፈጉ መሆኑን የፖለቲካ ሳይንስ መምህሩ ረዳት ፕሮፌሰር ዳምጠው ተሰማ ገለፁ።

የህግ ባለሞያው አቶ ተመስገን ገመቹ ደግሞ የቤንሻንጉል ጉሙዝ በተለይ የጉሙዝ ብሄር ተወላጆች

“መሬታችንን እንቀማ ይሆን?” የሚል ስጋት ወደ ግጭት ሊያስገባቸው ይችላል ይላሉ።

ረዳት ፕሮፌሰር ዳምጠው "የህወሓት ጣልቃ ገብነት በመተከል ችግር ውስጥ ድርሻ አለው ሲሉ አቶ ተመስገን ደግሞ "ችግራቸውን ወደ ውጭ አካል ከመጠቆም የክልሉ አመራሮች ራሳቸውን ማየት አለባቸው" ብለዋል።

"ዜጎች ላይ የሚደርሰው ግድያ እንዲቆምና መተከልን ለማረጋጋት ፖለቲካዊ መፍትሄ ያስፈልጋል" ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ምሁራኑ።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡

የባለሞያዎች አስተያየት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ስለሚስተዋሉ ግጭቶች
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:51 0:00


XS
SM
MD
LG